Olafscholz

የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሹልዝ አዲስ አበባ ገቡ

የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሹልዝ አዲስ አበባ ገቡ

የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሹልዝ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል። መራሄ መንግሥቱ የጀርመን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ፣ ባለሀብቶችን፣ የተቋማት መሪዎችን እንዲሁም በርከት ያለ የልዑካን አባላትን አስከትለው ነው ቦሌ አየር ማረፊያ የደረሱት። ሹልዝ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የመራሄ መንግሥቱን የሥራ ጉብኝት አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በሰጡት መግለጫ፤ ጉብኝቱ ታሪካዊና ጠንካራ የኹለትዮሽ ግንኙነት ላላቸው ኢትዮጵያና ጀርመን ከፍ ያለ ፋይዳ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ትብብሮችን ለማሳደግ ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማላቅ  የመራሄ መንግሥት ሹልዝ ጉብኝት ትርጉም ያለው መሆኑንም ገልጸዋል። መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጽያ ቆይታቸው…
Read More
የጀርመን መራሂ መንግሥት ኢትዮጵያን ሊገበኙ ነው

የጀርመን መራሂ መንግሥት ኢትዮጵያን ሊገበኙ ነው

የጀርመን መራሂ መንግስት በሚቀጥለው ሣምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ። የጀርመኑ የጀርመን መራሂ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በሚቀጥለው ሣምንት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተገለጸ፡፡ የጀርመን መራሂ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በውይይታቸውም ፥ ስለሰላም ስምምነቱ አተገባበር እንዲሁም አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች በተለይም በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገው ይመክራሉ ተብሏል፡፡ የአውሮፓ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ የሆነችው ጀርመን ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ድጋፍ ከሚያደርጉ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ዋነኛው ሀገር ነች።
Read More