29
Apr
የጀርመን መራሂ መንግስት በሚቀጥለው ሣምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ። የጀርመኑ የጀርመን መራሂ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በሚቀጥለው ሣምንት ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተገለጸ፡፡ የጀርመን መራሂ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በውይይታቸውም ፥ ስለሰላም ስምምነቱ አተገባበር እንዲሁም አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች በተለይም በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገው ይመክራሉ ተብሏል፡፡ የአውሮፓ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ የሆነችው ጀርመን ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ድጋፍ ከሚያደርጉ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ዋነኛው ሀገር ነች።