Amharicmusic

ዝነኛው የኢትዮጵያ ሙዚቀኛ ማሕሙድ አሕመድ ከመድረክ ሊሰናበት ነው

ዝነኛው የኢትዮጵያ ሙዚቀኛ ማሕሙድ አሕመድ ከመድረክ ሊሰናበት ነው

በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያደረገው ጋሽ ማህሙድ አህመድ ማይኩን ሊሰቅል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ማህሙድ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ዕድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የክቡር ዶክተር ማዕረግን መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፍ ዝነኛ  የሆነውን የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም የመሰናበቻ ፕሮግራም በአዲ አበባ እና በአሜሪካ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል፡፡ የመሰናበቻ ሙዚቃ ፕሮግራም ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲ አበባ ሚለኒየም አዳራሽ የድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የመጨረሻ የህይወት ዘመን ስንብት ደማቅ ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ተነግሯል ፡፡ በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይም የክቡር ዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ላይ የተዘጋጀ መፅሀፍ እንደሚመረቅም ተገልጿል፡፡…
Read More
የድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበም በ17 ሚሊዮን ብር ተሸጠ

የድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበም በ17 ሚሊዮን ብር ተሸጠ

መጠሪያዬ የተሰኘው የድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበም በኢትዮጵያ ታሪክ ውዱ አልበም ተብሏል ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበሟ ነሃሴ 23  ለአድማጮች እንደሚደርስ ድምጻዊቷ በዛሬው ዕለት በሰጠችው ጋዜጣዊ  መግለጫ ላይ ተናግራለች። መጠሪያዬ የሚል ስያሜ ያለው ይህ አዲ የሙዚቃ አልበም  የድምጻዊቷ  የመጀመሪያ አልበሟ ሲሆን  አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቅ 6 ሚሊዮን ብር እንደፈጀባት ተናግራለች፡፡ በመሆኑም የተጠናቀውን  ሙሉ አልበም በ160ሺ የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ17 ሚሊየን ብር በላይ መሸጡን በመግለጫው ለይ ተናግራለች። ይህ ክፍያ በኢትዮጵያ  ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑም ተጠቁሟል። አልበሙ በተለያዩ  አማራጮች ለአድማጭ የደረሰ ሲሆን ይህም በቴሌግራም ካሴት መተግበሪያ ላይ ፣ በራሷ የዩቲውብ ቻናል እና በዞጃክ  ዓለም አቀፍ  መተግበሪያዎች ላይ እንደሚለቀቅ ተናግራለች። አልበሙን የገዛው "Zojak worldwide" የተሰኘው የአሜሪካ አሳታሚ ድርጅት…
Read More
የሞስኮ ትምህርት ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት አማርኛ እና ስዋህሊ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምሩ ገለጹ

የሞስኮ ትምህርት ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት አማርኛ እና ስዋህሊ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምሩ ገለጹ

ሩሲያ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ አማርኛ እና ስህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ትምህርተ ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻ ነበር። በዚህም መሰረት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መስከረም በሞስኮ የሚገኙ ትምህ ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማስተማር ይጀመራል ሲል የሞስኮ ትምህርት እና ሳይንስ ክፍል አስታውቋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ 1517 የተሰኘው የፔዳጎጂ ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል ተብሏል። እንዲሁም 1522 የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል። ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች። ሩሲያ በቀጣይም በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር…
Read More
ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበሙን በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ ተከለከለ

ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበሙን በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ ተከለከለ

በኦሮሚኛ እና አማርኛ የሙዚቃ ስራዎቹ የሚታወቀው ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም ለቋል። "እንዳባቴ እወድሻለሁ" በሚል ለገበያ ያቀረበው ይህ የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም በገበያ ላይ በመሸጥ ላይ መሆኑን አስታውቋል። ድምጻዊው በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳለው ምክኒያቱ ባልተገለጸበት ሁኔታ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ መከልከሉን ገልጿል። "እንደ አባቴ እወድሻለሁ" የተሰኘዉ አልበም በማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ላይ በይፋ የተለቀቀ ቢሆንም በአዲስ አበባ ሲዲዉን የሚያዞሩ ወጣቶች መሸጥ እንዳይችሉ በፖሊስ መከልከላቸውንም ጠቅሷል። በትናንትናው እለት ሲዲዉን ለመሸጥ የወጡ ወጣቶች ከተከለከሉ በኋላም ድምፃዊዉ ክልከላዉ ለምን እንደተላለፈ አላዉቅም ብሏል። ድምፃዊዉ "ሁሉም ሰዉ ለኔ እኩል ነዉ ፤ በእኩልነት በአብሮነት ፣ በአንድነት የማምን ሰዉ ነኝ ያንን ሀሳብ ነዉ በአልበሜ ላይ ለማንጸባረቅ የሞከርኩት" ብሏል።…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም እና ሰዋሰው መተግበሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሰዋሰው መተግበሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

በእለቱ አብነት አጎናፍርን ጨምሮ የሁለት አርቲስቶች የአልበም ምርቃት፣ የክብር ስጦና እና የፊርማ ስነ ስርአትም ተከናውኗል። ሀገር በቀሉ የሙዚቃ አገልግሎት ሰጪው “ሰወሰው” መተግበሪያ ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል። የስምምነት ፊርማው በሰዋሰው መተግበሪያ እና በሰዋሰው ዩትዩብ ቻናል በኩል የሚሰራጩ የኪነ-ጥበብ ሥራዎችን የቅጂ መብት ለማስከበር ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል ። ይህ ስምምነት የኪነ-ጥበብ ስራዎቹ ተደራሽነት ላይም ትርጉም ያለው ለውጥ እንደሚፈጥር ተገልጿል። የመዝናኛውን ኢንዱስትሪ ዲጅታላይዝ በማድረግ በኩል አሻራውን በማሳረፍ ላይ የሚገኘው ሰዋሰው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በገባው ስምምነት ከነበሩት የክፍያ አማራጮች በተጨማሪ ወደ 9107 አጭር ቁጥር A ወይም B ብሎ በመላክ እለታዊ እና ሳምንታዊ የክፍያ የደንበኝነት ጥቅሎችን በመግዛት ደንበኞች የሚፈልጉትን ሙዚቃ እንዲያገኙ ያስችላል።…
Read More