Ethiopiamusic

ዝነኛው የኢትዮጵያ ሙዚቀኛ ማሕሙድ አሕመድ ከመድረክ ሊሰናበት ነው

ዝነኛው የኢትዮጵያ ሙዚቀኛ ማሕሙድ አሕመድ ከመድረክ ሊሰናበት ነው

በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያደረገው ጋሽ ማህሙድ አህመድ ማይኩን ሊሰቅል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ማህሙድ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ዕድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የክቡር ዶክተር ማዕረግን መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፍ ዝነኛ  የሆነውን የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም የመሰናበቻ ፕሮግራም በአዲ አበባ እና በአሜሪካ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል፡፡ የመሰናበቻ ሙዚቃ ፕሮግራም ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲ አበባ ሚለኒየም አዳራሽ የድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የመጨረሻ የህይወት ዘመን ስንብት ደማቅ ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ተነግሯል ፡፡ በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይም የክቡር ዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ላይ የተዘጋጀ መፅሀፍ እንደሚመረቅም ተገልጿል፡፡…
Read More
ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበሙን በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ ተከለከለ

ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበሙን በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ ተከለከለ

በኦሮሚኛ እና አማርኛ የሙዚቃ ስራዎቹ የሚታወቀው ድምፃዊ አቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም ለቋል። "እንዳባቴ እወድሻለሁ" በሚል ለገበያ ያቀረበው ይህ የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም በገበያ ላይ በመሸጥ ላይ መሆኑን አስታውቋል። ድምጻዊው በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳለው ምክኒያቱ ባልተገለጸበት ሁኔታ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ መከልከሉን ገልጿል። "እንደ አባቴ እወድሻለሁ" የተሰኘዉ አልበም በማህበራዊ መገናኛ መንገዶች ላይ በይፋ የተለቀቀ ቢሆንም በአዲስ አበባ ሲዲዉን የሚያዞሩ ወጣቶች መሸጥ እንዳይችሉ በፖሊስ መከልከላቸውንም ጠቅሷል። በትናንትናው እለት ሲዲዉን ለመሸጥ የወጡ ወጣቶች ከተከለከሉ በኋላም ድምፃዊዉ ክልከላዉ ለምን እንደተላለፈ አላዉቅም ብሏል። ድምፃዊዉ "ሁሉም ሰዉ ለኔ እኩል ነዉ ፤ በእኩልነት በአብሮነት ፣ በአንድነት የማምን ሰዉ ነኝ ያንን ሀሳብ ነዉ በአልበሜ ላይ ለማንጸባረቅ የሞከርኩት" ብሏል።…
Read More