01
Apr
የሮያሊቲ ክፍያ ከመጪው ሐምሌ ወር ጀምሮ መክፈል ይጀመራል ተብሏል የሙዚቀኞች የሮያለቲ ክፍያ ከሀምሌ ወር ጀምሮ መክፈል እንደሚጀመር ተገልጿል። መገናኛ ብዙሀን ለሙዚቀኞች የሮያሊቲ ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያስገደደው መመሪያ የፊታችን ሀምሌ 1ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። የሮያሊቲ ክፍያ ረቂቅ መመሪያው የሚመለከታቸው አካላትን ባሳተፈ መንገድ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን ህጉን ለማስፈጸም ስልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ቢበዛ ከአምስት ወር በኃላ ፀድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል ተናግረዋል። በኢትዮጲያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን አማካኝነት የተሰናደው ይህ ውይይት፣ሙዚቀኞች፣ ፕሮዲውሰሮች፣ደራሲያን እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል። ውይይቱ በዋናነት በሙዚቀኞች ሮያሊቲ ክፍያ ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የክፍያ ቀመር ተዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ…