19
Aug
መጠሪያዬ የተሰኘው የድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበም በኢትዮጵያ ታሪክ ውዱ አልበም ተብሏል ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበሟ ነሃሴ 23 ለአድማጮች እንደሚደርስ ድምጻዊቷ በዛሬው ዕለት በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግራለች። መጠሪያዬ የሚል ስያሜ ያለው ይህ አዲ የሙዚቃ አልበም የድምጻዊቷ የመጀመሪያ አልበሟ ሲሆን አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቅ 6 ሚሊዮን ብር እንደፈጀባት ተናግራለች፡፡ በመሆኑም የተጠናቀውን ሙሉ አልበም በ160ሺ የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ17 ሚሊየን ብር በላይ መሸጡን በመግለጫው ለይ ተናግራለች። ይህ ክፍያ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑም ተጠቁሟል። አልበሙ በተለያዩ አማራጮች ለአድማጭ የደረሰ ሲሆን ይህም በቴሌግራም ካሴት መተግበሪያ ላይ ፣ በራሷ የዩቲውብ ቻናል እና በዞጃክ ዓለም አቀፍ መተግበሪያዎች ላይ እንደሚለቀቅ ተናግራለች። አልበሙን የገዛው "Zojak worldwide" የተሰኘው የአሜሪካ አሳታሚ ድርጅት…