03
Dec
በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያደረገው ጋሽ ማህሙድ አህመድ ማይኩን ሊሰቅል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ማህሙድ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ዕድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የክቡር ዶክተር ማዕረግን መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፍ ዝነኛ የሆነውን የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም የመሰናበቻ ፕሮግራም በአዲ አበባ እና በአሜሪካ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል፡፡ የመሰናበቻ ሙዚቃ ፕሮግራም ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲ አበባ ሚለኒየም አዳራሽ የድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የመጨረሻ የህይወት ዘመን ስንብት ደማቅ ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ተነግሯል ፡፡ በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይም የክቡር ዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ላይ የተዘጋጀ መፅሀፍ እንደሚመረቅም ተገልጿል፡፡…