Blog

ግብጽ የህዳሴው ግድብን ዓለም አቀፋዊ ከማድረግ እንድትታቀብ ኢትዮጵያ አሳሰበች

ግብጽ የህዳሴው ግድብን ዓለም አቀፋዊ ከማድረግ እንድትታቀብ ኢትዮጵያ አሳሰበች

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ግብጽ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ተደጋጋሚ መግለጫዎችን እያወጣች ነው። መግለጫዎቹ ኢትዮጵያ በቀጣይ ክረምት ወራት ግድቡ ውሀ እንዲይዝ የተናጠል ውሳኔ እንዳትወስን የሚያሳስቡ ናቸው። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ከጋዜጠኞች ለቀረበው ጥያቄ "ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ውሀ አሞላል ዙሪያ ማንንም የማስፈቀድ ግዴታ የለባትም" ብለዋል። ታላቁ የህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ግዛት እና ሀብት እየተገነባ ያለ ፕሮጀክት ነው የሚሉት አምባሳደር መለስ በእቅዳችን እና በፕሮግራማችን እንመራለን ሲሉም አክለዋል። የግብጽ ሰሞንኛ ተደጋጋሚ መግለጫ የህዳሴው ግድብ አራተኛ ዙር ውሀ መመሙያ ጊዜ እየተቃረበ መምጣቱን ተከትሎ ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ ያለመ እንደሆነም ቃል አቀባዩ…
Read More
እነ ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነጻ ተሰናበቱ

እነ ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ ከተከሰሱበት የሙስና ወንጀል በነጻ ተሰናበቱ

ዶ/ር ሙሉቀን ሐብቱን ጨምሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሐብቱን ጨምሮ ከጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ግለሰቦች በነጻ አሰናብቷቸዋል፡፡  ፍርድ ቤቱ ብይኑን የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 4፤ 2015 በዋለው ችሎት ነው፡፡  በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፤ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ በፍርድ ቤቱ በይኗል። ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው፤ “ዐቃቤ ህግ ባቀረበው የሰው…
Read More
ግዙፉ የቻይና ኩባንያ በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ፋብሪካ መገንባት እንደሚፈልግ ገለጸ

ግዙፉ የቻይና ኩባንያ በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ፋብሪካ መገንባት እንደሚፈልግ ገለጸ

በቻይና በሲሚንቶ ዘርፍ የተሰማራው ግዙፉ ሲኖማ ዓለም አቀፍ ኩባንያ በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ፋብሪካ መገንባት እንደሚፈልግ ገልጿል። በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው የሲኖማ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ሊቀመንበር እና የሲኤንቢኤም ተቋም ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ሚስተር ሉ ያን እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ተወያይተዋል። ኩባንያው በኢትዮጵያ ኢንቨስት በሚደረግበት ዙሪያ ቤጂንግ በሚገኘው የኩባንያው ዋና ጽ/ቤት ተገኝተው ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ተፈራ በውይይቱ ወቅት ኩባንያው በኢትዮጵያ ባሉት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከዲዛይን ጀምሮ በግንባታ ረገድ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ በኢትዮጵያ ካለው የግንባታ ስፋት አንጻር የሲሚንቶ ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። አምባሳደር ተፈራ አያይዘውም፣ ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የሲሚንቶ ፍላጎት ግምት ውስጥ በማስገባት በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ቢሰማራ የጋራ ተጠቃሚነቱ ሰፊ መሆኑን ገልጸዋል።…
Read More
በደብረ ብርሃን መከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማዋ እንዳይገባ በሚል የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ

በደብረ ብርሃን መከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማዋ እንዳይገባ በሚል የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ

ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በሚያስኬደው ዋና መንገድ ደብረ ብርሃን ከተማ አቅራቢያ በመከላከያ እና የመንግሥትን ውሳኔ ባልተቀበሉ ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ይገኛል። የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው "መከላከያ ያልፋል አያልፍም" በሚል አለመግባባት መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢትዮ ነጋሪ ተናግረዋል። ተኩሱ ከተጀመረ አንድ ሰዓት ያለፈው ሲሆን፤ የተኩስ ልውውጡ ዳሸን ቢራ ፋብሪካ አካባቢ የሚገኙ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና "ፋኖ" በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ኃይል እና በመከላከያ መካከል እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የከተማዋ እና የአካባቢው ነዋሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሀይሎችን ትጥቅ ያስፈታል በሚል አዳራቸውን ሲጠብቁ እንዳደሩ እና ዛሬ ረፋድ ጀምሮ ግን የተኩስ ልውውጡ መጀመሩን ከነዋሪዎች ሰምተናል፡፡ በከተማዋ የመንግስትን እቅድ ተቃውሞ መጀመሩን ተከትሎ ትናንት እና ዛሬ የግል…
Read More
በአጣዬ ዙሪያ ዳግም ጦርነት ተነሳ

በአጣዬ ዙሪያ ዳግም ጦርነት ተነሳ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሚያ ብሄረሰብ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢዎች ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ጦርነት መጀመሩን የአይን እማኞች ለኢትዮ ነጋሪ ገልጸዋል፡፡ በኦሮሞ በሄረሰብ ዞን ስር ካሉ ወረዳዎች መካከል አንዱ ከሆነው ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሰንበቴ ከተማ የተነሱ ታጣቂዎች ወደ ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ስራ ካለችው አላላ ቀበሌ በመሄድ የሰብል ስብሰባ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ነዋሪዎቹ አክለዋል፡፡ ተኩሱን ተከትሎም ወደ አካባቢው ባሉ ሌሎች ቀበሌዎች ጦርነት የተጀመረ ሲሆን ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ጥለው ተሰደዋል ተብሏል፡፡ በአካባቢው የነበረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጦርነቱን ለማስቆም ሞክሮ እንዳልተሳ የነገሩን ነዋሪዎቹ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ተጨማሪ ሀይል ከአጎራባች አካባቢዎች በመግባት ላይ ነውም ብለውናል፡፡ ከሁለት ወር በፊት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ…
Read More
በአማራ ክልል ለሶስተኛ ቀን ተቃውሞ ቀጥሏል

በአማራ ክልል ለሶስተኛ ቀን ተቃውሞ ቀጥሏል

በአማራ ክልል ለሶስተኛ ቀን ተቃውሞ ቀጥሏል የፌደራል መንግሥት የተማከለ የጸጥታ ሀይል ለመመስረት ማቀዱን ተከትሎ የክልል ልዩ ሀይሎች እንዲፈርሱ ውሳኔ አስተላልፏል። ህጋዊ መሰረት የለውም የሚባለው የክልል ልዩ ሀይል አባላት ወደ ፌደራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ እና መደበኛ ፖሊስ እንዲደራጁም ትግበራ መጀመሩን የፌደራል መንግሥት አስታውቋል። ይሁንና በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የመንግሥትን ውሳኔ የተጠራጠሩ እና የተቃወሙ ሰዎች ወደ አደባባይ ለተቃውሞ ወጥተዋል። በተለይም በሰሜን ወሎ፣ ጎጃም እና ሌሎችም አካባቢዎች መንገዶች በተቃዋሚዎች የተዘጉ ሲሆን ወደ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚያስገቡ መንገዶችም ተዘግተዋል። ይህን ተከትሎም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል የሚያስኬዱ መንገዶች በከፊል ተዘግተዋል። ህዝቡ ወደ አደባባይ የወጣው የትግራይ…
Read More
በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳሩ ወደ አስቸጋሪ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ የፓለቲካ ምህዳሩ ወደ አስቸጋሪ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ የስነ መንግስት ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት የፓለቲካ ምዕራፍ እጅግ  አስቸጋሪ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርታ (ኢዜማ) ዋና ፀሐፊ አበበ አካሉ ገልፀዋል። አቶ አበበ አካሉ ይሄን በእናት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ እየገባ ነው። በኢትዮጵያ እየተሸጋገረ የመጣውን አደገኛ የፓለቲካ ምዕራፍ በተበታተነ ትግል ውስጥ መቀልበስ እንደማይቻልም አቶ አንስተዋል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ቅንጦት ነው የሚሉት አቶ አበበ ሰውነት እጅግ የረከሰበት ዘመን ላይ መድረሳቸውን አስታውሰዋል። አክለውም የአገር እሴት ሲናድ አብሮ የሚናድ አገረ መንግስት ምስረታ በመኖሩ የሀገርን ቋሚ እሴት'ና ምዕተ አመት ዘለል ተቋማት መከበር አለባቸው ብለዋል። ምንም እንኳን እንደ ፓርቲ ህገመንግስቱ እንዲቀየር…
Read More
ሞ ፋራህ የፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ውድድርን በሰባተኛነት አጠናቀቀ

ሞ ፋራህ የፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ውድድርን በሰባተኛነት አጠናቀቀ

በሳሙኤል አባተ ሞ ፋራህ በፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ውድድርን በሰባተኛነት አጠናቀቀ። ሞ ፋራህ የጋቦን ፖርት-ጄንቲል 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በ30 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ ሰባተኛ ሆኖ አጠናቋል። የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነው ሞ ፋራህ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚካሄደው የለንደን ማራቶን ውድድር በኢትዮጵያ ልምምዱን አድርጓል ተብሏል። አትሌቱ 2023 ጡረታ ከመውጣቱ በፊት የመጨረሻው የውድድር ዓመቱ እንደሚሆን ባለፈው በጥር ወር አስታውቋል። ጋቦን ላይ ኬንያዊው ቪንሴንት ኪፕኬሞይ በ28 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ አንደኛ በመውጣት አሸንፏል። ፋራህ እ.ኤ.አ. በ2022 የለንደን ማራቶን በሽንጥ ጉዳት ምክንያት ያልተሳተፈ ሲሆን፤ የዘንድሮው ውድድር ከ2019 በኋላ የመጀመሪያው ሙሉ ማራቶን ይሆናል ተብሏል። ለብሪታኒያዊው የመጨረሻ የለንደን ማራቶን ውድድር እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን፤ ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ በታሪክ…
Read More
የኢትዮጵያ ትልቁ ባንክ ከቻይናው የቴክስታይል ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ትልቁ ባንክ ከቻይናው የቴክስታይል ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ የደንብ ልብስ ከሚያቀርብ የቻይና ቴክስታይል ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሠራተኞቹ የደንብ ልብስ አቅርቦት ከቻይናው ጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ ጋር መፈራረሙን አስታውቋል። የንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ጥራት ያለው የደንብ ልብስ ለሠራተኞች እንዲቀርብ የሚያስችል ውይይት ከጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ ተወካዮች ጋር መወያየታቸው ተመላክቷል፡፡ ለደንብ ልብስ አቅርቦቱ ባንኩ ከፍተኛ ወጪ በመመደብ ለአብዛኛው ሠራተኛ ወጪውን የሸፈነ ሲሆን፣ በመካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የባንኩ ሠራተኞች እንዲሁም የሥራ ኃላፊዎች ደግሞ የተወሰነ ወጪ ተጋርተው የሚቀርብ መሆኑን አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡ የጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚ/ር ጋዊ ቻንሁሀ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ደንብ ልብስ ተቋማቸው በኢትዮጵያ ቅርንጫፉ ከሚሰራቸው አቅርቦቶች ትልቁ…
Read More
ሸራተን ሆቴል በጅማ ከተማ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል ሊገነባ ነው

ሸራተን ሆቴል በጅማ ከተማ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል ሊገነባ ነው

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር ያለው ሸራተን ሆቴል በ ጅማ ከተማ በፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ደረጃ ባለ አምስት ኮከብ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል:: የግንባታ መሰረተ ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ አስቀምጠዋል፡፡ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዚህ በፊት ጅማ ከተማ ኖክ ማደያ አካባቢ ለመገንባት አቅዶ የነበረውን ፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ዘመናዊ ሆቴል ወደ ከተማዋ መግቢያ እንዲዛወር ተደርጓል። ከዚህ በፊት ሆቴሉ ሊገነባበት የነበረው ቦታ ላይም ዘመናዊ የገበያ ማዕከል እንደሚገነባም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ኩባንያ አቶ ጀማል አህመድ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ክልል ሰፊ…
Read More