27
Apr
አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመረጠች የኮንፌዴሬሽን ኦፍ አፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ በዛምቢያ መዲና ሉሳካ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንድትመራ ተመርጣለች፡፡ በዚህም ካውንስሉ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንድትመራ በሙሉ ድምጽ መመረጧን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ የ51 ዓመቷ አትሌት ደራርቱ ሀገሯን እና ራሷን ያስጠራችባቸው በርካታ ሜዳሊያዎችን ያሸነፈች ሲሆን በኦሎምፒክ የ10 ሺህ ሜትር ርቀት ውድድር ታሪክ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጣች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ ተብላለች፡፡ አትሌት ደራርቱ ከ2018 ጀምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ከቀድሞው ፕሬዝዳንት አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ተረክባ በመምራት ላይ ትገኛለች፡፡ አትሌቷ ባሳካቻቸው በርካታ ውድድሮች ለሌሎች ታዳጊ አትሌቶች…