29
Jan
የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር የስድስት ወራት ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ አለሙ ስሜ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ የሚደረገው ክልከላ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ አቶ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ለፓርላማው እንደተናገሩት፥ ነዳጅ የሚወስዱ ተሽከርካሪዎችን ለግል ጥቅማጥቅ ሆነ ለሌላ አላማ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚደረገውን እገዳ በጥብቅ እንደሚያስፈጽሙ ገልጸዋል። ውሳኔው ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ስጋቶች እና ከባህላዊ የነዳጅ ፍጆታ ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለሚመጣው ወጭ ስልታዊ ምላሽ ነውም ተብሏል። እየጨመረ የመጣው የነዳጅ ወጪ ፖሊሲ አውጪዎች አገሪቱ በተለመዱት ተሽከርካሪዎች ላይ ያላትን ጥገኝነት እንዲገመግሙ እና የካርበን በካይ ጋዝ መጠንን ለመቀነስ ከሚደረገው…