23
Oct
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ ምርጫ፤ በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለማድረግ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል። የምርጫ ውጤት ለህዝብ ማሳወቂያ ቀን ደግሞ ሰኔ 3 ቀን እንደሚሆንም ቦርዱ አስታውቋል። ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኘው ብሔራዊው ምርጫ ቦርድ በምርጫው የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አድርጓል። ከ60 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በተሳተፉበት በዚህ ውይይት ላይ በምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ላይ የጦፈ ውይይት መደረጉ ተገልጿል። መገናኛ ብዙሃን ባልተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ፤ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳን ለፓርቲዎች ለውይይት አቅርቧል። ለውይይት በቀረበው የጊዜ ሰሌዳው መሰረትም ህዳር ወር ውስጥ በምርጫ መወዳደር የሚፈልጉ…