ዜና

ዶክተር ዮሀንስ አያሌው የጸደይ ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

ዶክተር ዮሀንስ አያሌው የጸደይ ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

የቀድሞው ልማት ባንክ እና አማራ ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሀንስ አያሌው በኪሳራ ላይ ላለው ጸደይ ባንክ ፕሬዝዳንት ተደርገው ተሾመዋል። የአማራ ብድርና ቁጠባ ድርጅት በሚል ሲጠራ የነበረው በኋላም ጸደይ ባንክ በሚል ስያሜ የኢትዮጵያን የባንክ ቢዝነስ የተቀላቀለው ጸደይ ባንክ በኪሳራ ላይ ይገኛል። ባንኩ በ2024/25 በጀት ዓመት ብቻ የሁለት ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት ከአንድ ወር በፊት ዓመታዊ ጉባኤውን ሲያካሂድ ገልጿል። ይህን ተከትሎም ዶክተር ዮሀንስ አያሌው የባንኩ አዲስ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተሾሙለት ባንኩ ከደቂቃዎች በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስታውቋል። በኪሳራ ላይ ያሉ የገንዘብ ድርጅቶችን በመታደግ የሚታወቁት ዶክተር ዮሀንስ ከዚህ በፊት ልማት ባንክን እንዲሁም የአማራ ባንክን ከኪሳራ ወደ ትርፍ መመለሳቸው ይገለጿል። ላለፉት ዓመታት ጸደይ ባንክን በፕሬዝዳንትነት…
Read More
የኤርትራ ጦር ከአማጺ ጋር በመተባበር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱ ተገለጸ

የኤርትራ ጦር ከአማጺ ጋር በመተባበር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳስታወቀው ኤርትራ ባለፉት ቀናት አዲስ ወታደሮችን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን አስታውቋልል። ሚንስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ለኤርትራ አቻቸው ኦስማን ሳሌህ በጻፉት ደብዳቤ የኤርትራ ጦር ከአማጺያን ጋር በመተባበር በሰሜን ምስራቅ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን አስታውቋል። ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የኤርትራ ወታደሮችም ከአማጺያን ጋር በመቀናጀት ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆኑም ተገልጿል። በመሆኑም እነዚህ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ባስቸኳይ እንዲወጡም ጠይቋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በደብዳቤው ላይ ከኤርትራ ጋር የገቡበትን አለመግባባት በዲፕሎማሲ ለመፍታት ዝግጁ እንደሆነም ገልጿል። ሚንስትሩ አክለውም በተለይ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት እና የአሰብ ወደብን ለማግኘት ያቀረበቻቸውን ጥያቄዎች ጨምሮ ሌሎች ፍላጎቶችን ሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ለመወያየት ዝግጁ እንደሆነችም ተጠቅሷል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው…
Read More
የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸምን የሚከታተለው የባለሙያዎች ቡድን መቐለ ገባ

የፕሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸምን የሚከታተለው የባለሙያዎች ቡድን መቐለ ገባ

ለሁለት ዓመት የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲቆም ምክንያት የሆነው የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት አፈጻጸም የሚከታተል የባለሙያዎች ቡድን ትግራይ ክልል መቐለ መግባቱ ተገልጿል። ስምምነቱ እንዲፈረም ያደራደረው የአፍሪካ ህብረት የባለሙያዎችን ቡድን ያቋቋመው ከኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ እና አልጀሪያ የተውጣጡ ናቸው። ይህ የባለሙያዎች ቡድን በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታታቸውን፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች መቀጠላቸውን፣ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው መመለሳቸውን የመከታተል ሀላፊነት ተሰጥቶታል። ዛሬ መቐለ መድረሱ የተገለጸው ይህ የባለሙያዎች ቡድን መቀመጫውን መቐለ በማድረግ የስምምነቱን አፈጻጸም ሲከታተል የቆየ ሲሆን ላለፉት ወራት በዕረፍት ላይ መቆየቱን የትግራይ ሰላምና ደህንነት ቢሮ አስታውቋል። ይህ የባለሙያዎች ቡድን ከአስተዳድራዊ ዕረፍት በኋላ ወደ መቐለ የተመለሰው በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ…
Read More
በኒጀር የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች የሽብር ጥቃት ደረሰባቸው

በኒጀር የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች የሽብር ጥቃት ደረሰባቸው

አየር መንገዱ እንደገለጸው ባለፈው ሃሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ አውሮፕላን ማረፊያ በደረሰው ጥቃት ሁለት የአስካይ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል። ሁለቱ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አጋር የሆነው የአስካይ  አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት ከአውሮፕላን አከራዮች የተከራያቸው እና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የተመዘገቡ ናቸው ተብሏል። በአውሮፕላኖቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም የተላከው የቴክኒክ ቡድን ጉዳቱ መጠነኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ የገለጸው አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹ ተጠግነው በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሎሜ (ቶጎ) መቀመጫውን ካደረገው አስካይ አየር መንገድ ጋር የ40% የባለቤትነት ድርሻና የቴክኒክ አጋርነት አለው። የአስካይ አውሮፕላኖች የሽብር ጥቃት ኢላማ…
Read More
በአላማጣ እና አካባቢው በተፈጠረው አዲስ ግጭት ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

በአላማጣ እና አካባቢው በተፈጠረው አዲስ ግጭት ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከጥር 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች አንዳንድ አዋሳኝ አካባቢዎች ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል። በዚህም ይህ መግለጫ ይፋ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ በተለይም በጸለምት/ጠለምት፣ በመጋሌ እና አብአላ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን ተከትሎ የሰዎችን የሕይወት፣ የአካል ደኅንነት፣ ነጻነት እና ንብረት መብቶች ሥጋት ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ተብሏል፡፡ በተጠቀሱት አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ግጭት እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ወደ ጦርነት ሊሸጋገር ይችላል የሚል ሥጋት በመፈጠሩ ሳቢያ ነዋሪዎች ‘በኮማንድ ፖስት’ ሲተዳደሩ ከቆዩት አላማጣ ከተማ እና ሌሎች አካባቢዎች የተፈናቀሉ መሆኑን እንዲሁም በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ ገደቦች መጣላቸውን ኢሰመኮ ገልጿል፡፡ ይህ ግጭት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተከትሎ…
Read More
ፓርላማው የሞርጌጅ ባንክ ዳግም እንዲቋቋም ጠየቀ

ፓርላማው የሞርጌጅ ባንክ ዳግም እንዲቋቋም ጠየቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሞርጌጅ ባንክ ወይም የቤት ብድር ባንክን ሀላፊነት ወስዶ መልሶ እንዲያደራጅ ጠይቋል፡፡ በሀገሪቱ ቀድሞ የነበረዉ የሞርጌጅ ባንክ ባልታወቀ ምክንያት ወደ ንግድ ባንክ መቀላቀሉ ስህተት መሆኑ ተገልጿል። ፓርላመው ይህን የተጠየቀዉ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ነው። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሠረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ መሃመድ አብዶ በግምገማዉ ወቅት መንግስት በቤቶች ልማት ላይ ያለውን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት የሞርጌጅ ባንክ መልሶ ማደራጀት አለበት ሲሉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ዘመናት የቤት ብድር ባንክ ሞርጌጅ እንደነበረና ባልታወቀ ምክንያት ፈርሶ ወደ ንግድ ባንክ የተቀላቀለ መሆኑን የቋሚ…
Read More
የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው አዲስ አበባ ገቡ

የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው አዲስ አበባ ገቡ

ላዳው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሌሎች የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ለመምከር ባደረጉት ጉዞ የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰንን አስከትለው አዲስ አበባ ገብተዋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው እና የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን በኢትዮጵያ አየር ኃይል የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የአቭዬሽን ኤክስፖ መጎብኘታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ ከምስል ጋር አጋርቷል። ኢትዮጵያ እና ግብጽን ጨምሮ አራት የአፍሪካ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ ያሉት ክርስቶፈር ላንዳው በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ላንዳው በዛሬው ዕለት የተመሰረተበትን 90ኛ ዓመት እያከበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ሀይል አቪዬሽን ኤክስፖ ጎብኝተዋል ተብሏል፡፡ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ…
Read More
ኢትዮጵያ የማርበርግ ወረርሽኝን መቆጣጠሯን አስታወቀች

ኢትዮጵያ የማርበርግ ወረርሽኝን መቆጣጠሯን አስታወቀች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረው የማርበርግ ቫይረስ (Marburg Viral Disease) ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ፣ ወረርሽኙ ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰቱ በይፋ ከተነገረበት ከሕዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሰፊ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። በወረርሽኙ ወቅት በአጠቃላይ ለ3 ሺህ 800 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው 14 ሰዎች ነበሩ። ከታካሚዎቹ መካከል ዘጠኙ በበሽታው ምክንያት ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ አምስቱ ደግሞ ተገቢውን ሕክምና አግኝተው ማገገም መቻላቸው ይታወቃል። ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር እንዲቻል የክትትልና ምላሽ ስርዓት ተዘርግቶ ሲሰራ መቆየቱን የገለጸው ሚኒስቴሩ በተለይም ከ4 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተጓዦች በመውጫና…
Read More
የጣልያኑ ሊሞንታ ስፖርት ኩባንያ በኢትዮጵያ ስታዲየሞችን ለማልማት ድርድር ጀመረ

የጣልያኑ ሊሞንታ ስፖርት ኩባንያ በኢትዮጵያ ስታዲየሞችን ለማልማት ድርድር ጀመረ

በዓለም እና ስፔን እግር ኳስ ታሪክ ቀዳሚ የሆነው የሪያል ማድሪድን ስታዲየም ቤርናቢዩ ሜዳ የሰራው ግዙፍ ተቋም በአዲስ አበባ ይገኛል። ተቀማጭነቱን በጣልያን ያደረገው ሊሞንታ ስፖርት (Limonta Sport) ለስፖርት ሜዳዎች የሚሆኑ ሰው ሰራሽ (Artificial) እና ቅልቅል (Hybrid) ሳሮችን በማምረት እና በማንጠፍ ታዋቂነትን ያተረፈ የስፖርት መሰረተ ልማት ተቋም ነው። በፊፋ እውቅና ያለው ይህ ተቋም ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። ኩባንያው በመላው ዓለም አርቴፊሻል እና ሃይብሪድ የስታዲየም ውስጥ ሳሮችን በማምረት ይታወቃል። ኩባንያው ከሚያመርታቸው የስታዲየም ውስጥ ሳር መካከል ድብልቁ ወይም ሀይብሪዱ 95 ከመቶው የተፈጥሮ ሳር ሲሆን 5 ከመቶው ደግሞ አርቲፊሻል ሴንቴቲክ ነው ። ሊሞንታ ኩባንያ የሚያነጥፈው እና የሚያበቅለው ሳሩ በዝናብ ወቅት ውሃን በ5 ደቂቃ ውስጥ የማፍሰስ ችሎታ…
Read More
የምርጫ ቦርድ አዲስ አሰራር ተፅዕኖ እንደሚፈጥርባቸዉ ፓርቲዎች አስታወቁ

የምርጫ ቦርድ አዲስ አሰራር ተፅዕኖ እንደሚፈጥርባቸዉ ፓርቲዎች አስታወቁ

ስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ የዘረጋው አዲስ አሰራር በቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጥርባቸው አስታውቀዋል። የቦርዱን አዲስ አሰራር የተቃወሙ ፓርቲዎች የህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ  ፓርቲ (ህብር ኢትዮጵያ)፣ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ( ባልደራስ) ትብብር ለኢትዮጵያ  አንድነት ፓርቲ፣ለኢትዮጵያ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ፓርቲዎች ናቸው። በዚህ በጋራ መግለጫቸው የሀገሪቱ አቅም ባልፈቀደበትና እንደ ሀገር  ግንዛቤ በሌለበት ቴክኖሎጂካል አሰራር  ለመስፈርትነት መጠቀም አግባብነት የለውም ብለዋል። አካል ጉዳተኞች ከሁለት ሆስፒታሎች ማስረጃ እንዲያቀርቡ ግዴታ መቀመጡ፣ የአገሪቱን ገጠር አካባቢዎች ያላገናዘበና ሆስፒታሎች በሌሉበት ማስረጃ  መጠየቅ የአካል ጉዳተኞች ነባራዊ ሁኔታ የሚዳሰስና የሚታይ ሆኖ ሳለ ማስረጃ መጠየቁ በራሱ…
Read More