26
Feb
በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት በቆየው ጦርነት ምክንያት ከተጎዱ ክልሎች መካከል አንዱ ትግራይ ሲሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ከመሞታቸው በተጨማሪ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ይህ ጦርነት በደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተደረገው የፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ጦርነቱ የቆመ ሲሆን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ዳግም ስራ ጀምረዋል፡፡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ከተቋቋመ በኋላ ከፌደራል መንግስት እና ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ተጎጂዎችን ለመርዳት እየተሰራም ይገኛል፡፡ ቀስ በቀስ ህይወት በትግራይ ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶች እየተካሄዱ ሲሆን ኢትዮ ነጋሪ ወደ ክልሉ አምርታ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ምልከታ አድርጋለች፡፡ ከታዘብናቸው ጉዳዮች መካከል ህይወት በትግራይ መዲና መቀሌ ምን ይመስላል? የሚለው ሲሆን የኑሮ…