airpollution

ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አገደች

ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አገደች

ከወራት ማመንታት በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ የግል አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ እገዳ መጣሉ ተገልጿል፡፡ መኪኖችን ከተለያዩ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት ስራ የተሰማሩ ኩባንያዎች እንዳሉት ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት እንደማይችሉ እንደተነገራቸው ተናግረዋል። ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ከአውሮፓና ደቡብ አፍሪቃ ያጓጓዟቸውን በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ማስገባት እንደማይችሉ ከሶስት ሳምንት በፊት ተነግሯቸዋል። በእገዳው ሳቢያ ከፍተኛ መጉላላትና ኪሳራ እንደደረሰባቸው ባለጉዳዮቹ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል። ከሳምንታት በፊት የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማገዱን ለፓርላማ አባላት ሲያስታውቅ የገንዘብ ሚኒስቴር በበኩሉ እገዳው ተገባራዊ እንደማይደረግና በዕቅድ ደረጃ ያለ መሆኑን ተናግሮ ነበር። ይሁንና ባለፉት ቀናት የተለየ ፍላጎት ላላቸው የልማት ፕሮጀክቶችና ለህዝብ ትራንስፖርት የሚውሉ ካልሆኑ በቀር በነዳጅ የሚሰሩ…
Read More