06
Mar
ከ13 ዓመት በፊት የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 95 በመቶ መድረሱን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የግድቡ አጠቃላይ የሲቪል ስራው ግንባታ የደረሰበት ደረጃ 98 ነጥብ 9 በመቶ ተጠናቋል የተባለ ሲሆን የኤሌክትሮ መካኒካ ስራው ደውም በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ከአፍሪካ ግዙፉ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴው ግድብ በአሁኑ ወቅት በሁለት ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት በማመንጨት ላይ ይገኛል፡፡ የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም የግድቡ ግንባታ የተጀመረበትን 13ኛ ዓመት አስመልክቶ እንደተናገሩት አሁን ላይ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተመረተ ያለው ኤሌትሪክ ኃይል በ2 ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት መሆኑን ያነሱ…