26
Mar
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሁለት ሳምንት በፊት ያጋጠመውን የሲስተም ችግር አስመልክቶ እያደረገ ያለውን ስራ የደረሰበት ደረጃ ላይ መግለጫ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በሰጡት መግለጫ፤ ችግሩ የት ጋር ነው ያጠመው የሚለው ላይ በባለሙያ ጥናት እየተደረገ ነው ገና አላለቀም ብለዋል። በእለቱ ከተፈጠረው የሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ በተደረጉ ግብይች እና የገንዘብ ዝውወሮች ዙሪያም ማብራሪያ ሰጥተዋል። በእለቱ ሊጠፋ የነበረ ወይም አንድ ሰው ገንዘብ ከአካውንቱ ገንዘብ ካስተላለፈ በኋላ ለተላከለትም ሰው ደርሶ ገንዘቡ ለላኪውም ተመለሶ የተተካ ወይም ሪቨርስ ያደረገ 801 ሚሊየን 417 ሺህ 800 ብር ነበር ብለዋል። በእለቱ አጋጥሞ በነበረ የሲስተም ችግር በነበረበት መስመር ላይ 25 ሺህ 761 ደንበኞች ገብይት ፈጽመዋል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤…