06
Apr
የኢትዮጵያ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ወይም ስታርት አፕ የተለያዩ ማበረታቻዎችን መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ለስራ ፈጣሪዎች ከተደረጉት ማሻሻያዎች መካከል ከግብር ነጻ እድል፣ ከውጭ ንግዶች የሚያገኟቸውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ሙሉ ለሙሉ እንዲወስዱ፣ ንግድ ፈቃድ ለማውጣት የግድ ቢሮ ያስፈልግ የነበረውን ማንሳት፣ አዲ ሀሳብ ላላቸው ብድር ማመቻቸት እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይህ አውደ ርዕይ ለ20 ቀናት ይቆያል የተባለ ሲሆን ጎብኚዎች ወደ ሳይንስ ሙዚየም በማቅናት መግባት እና መጎብኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል አንዱ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች ሃሳባቸውን ወደ ተግባር ለማዋል በሚፈልጉበት ወቅት…