06
Apr
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብተዋል ተብሏል። የአሰልጣኙን የመልቀቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እየተወያዩበት እንደሆነ ትርታ ስፖርት ዘግቧል። የስራ አስፈፃሚ አባላቱ በሁለት ሀሳብ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። አንዳንዶቹ አሁኑኑ ይሰናበት ጥያቄውን እንቀበል ያሉ ሲሆን ሌሎች አባላት ደግሞ ቀሪ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ይጨርስ እያሉ ይገኛሉ ተብላል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ ከአሰልጣኙ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ውሳኔውን የሚያሳውቅ ይሆናል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ልምድ ካላቸው አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በመሆን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ2020 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ…