11
Apr
ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በሚያስኬደው ዋና መንገድ ደብረ ብርሃን ከተማ አቅራቢያ በመከላከያ እና የመንግሥትን ውሳኔ ባልተቀበሉ ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ይገኛል። የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው "መከላከያ ያልፋል አያልፍም" በሚል አለመግባባት መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢትዮ ነጋሪ ተናግረዋል። ተኩሱ ከተጀመረ አንድ ሰዓት ያለፈው ሲሆን፤ የተኩስ ልውውጡ ዳሸን ቢራ ፋብሪካ አካባቢ የሚገኙ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና "ፋኖ" በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ኃይል እና በመከላከያ መካከል እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የከተማዋ እና የአካባቢው ነዋሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሀይሎችን ትጥቅ ያስፈታል በሚል አዳራቸውን ሲጠብቁ እንዳደሩ እና ዛሬ ረፋድ ጀምሮ ግን የተኩስ ልውውጡ መጀመሩን ከነዋሪዎች ሰምተናል፡፡ በከተማዋ የመንግስትን እቅድ ተቃውሞ መጀመሩን ተከትሎ ትናንት እና ዛሬ የግል…