specialneeds

በኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ ህገ-መንግታዊ እውቅና እንዲሰጠው ተጠየቀ

በኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ ህገ-መንግታዊ እውቅና እንዲሰጠው ተጠየቀ

ሩትስና ዊንግስ የተባለ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት የምልክት ቋንቋ በሚሊዮኖች ቢነገርም ተገቢውን እውቅና አላገኘም ብሏል። ከተመሰረተ ሁለት ዓመት የሞላው ድርጅቱ ይህም በመሆኑ መስማት የተሳናቸው ዜጎች በቋንቋቸው የመማር፣ የመገልገልና መረጃ የማግኘት መብታቸው እንደተገደበ ተናግሯል። የኢትዮጵያ የምልክት ቋንቋ እንደሌሎች ቋንቋዎች "ሀገርኛ" ቢሆንም እንዳላደገ ተነግሯል። የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ሰርካለም ግርማ (ዶ/ር) ለአል ዐይን  የምልክት ቋንቋ በቋንቋ ፖሊሲው እንዲካተት ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።ፖሊሲው ገና ባለመጽደቁ "ተስፈኞች" ነን ብለዋል። ከ90 በመቶ በላይ የምልክት ቋንቋ ተናጋሪዎች ቋንቋቸውን የሚማሩት ት/ቤት ቢሆንም ሀገሪቱ ካሏት ት/ቤቶች አንድ በመቶ የማይሞሉት ብቻ 'አካቶ ትምህርት የሚያስተምሩ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት እያሱ ኃይሉ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ቋንቋው እንዲያድግና ትኩረት እንዲሰጠው የሀገሪቱ የስራ…
Read More