07
Apr
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር ያለው ሸራተን ሆቴል በ ጅማ ከተማ በፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ደረጃ ባለ አምስት ኮከብ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል:: የግንባታ መሰረተ ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ አስቀምጠዋል፡፡ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከዚህ በፊት ጅማ ከተማ ኖክ ማደያ አካባቢ ለመገንባት አቅዶ የነበረውን ፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ዘመናዊ ሆቴል ወደ ከተማዋ መግቢያ እንዲዛወር ተደርጓል። ከዚህ በፊት ሆቴሉ ሊገነባበት የነበረው ቦታ ላይም ዘመናዊ የገበያ ማዕከል እንደሚገነባም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ኩባንያ አቶ ጀማል አህመድ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ክልል ሰፊ…