08
Apr
በኢትዮጵያ የስነ መንግስት ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት የፓለቲካ ምዕራፍ እጅግ አስቸጋሪ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርታ (ኢዜማ) ዋና ፀሐፊ አበበ አካሉ ገልፀዋል። አቶ አበበ አካሉ ይሄን በእናት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳሉት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ እየገባ ነው። በኢትዮጵያ እየተሸጋገረ የመጣውን አደገኛ የፓለቲካ ምዕራፍ በተበታተነ ትግል ውስጥ መቀልበስ እንደማይቻልም አቶ አንስተዋል። አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ቅንጦት ነው የሚሉት አቶ አበበ ሰውነት እጅግ የረከሰበት ዘመን ላይ መድረሳቸውን አስታውሰዋል። አክለውም የአገር እሴት ሲናድ አብሮ የሚናድ አገረ መንግስት ምስረታ በመኖሩ የሀገርን ቋሚ እሴት'ና ምዕተ አመት ዘለል ተቋማት መከበር አለባቸው ብለዋል። ምንም እንኳን እንደ ፓርቲ ህገመንግስቱ እንዲቀየር…