ዜና

በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት 15 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት መውደሙ ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለው ጦርነት ምክንያት 15 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት መውደሙ ተገለጸ

ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡ ይህ ግጭት ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ወደ ጦርነት የተቀየረ ሲሆን የቀድሞው የክልሉ መንግስት በመደበኛ የክልሉ የጸጥታ ሀይል ህግ ማስከበር እንደማይችል እና የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ በደብዳቤ ጠይቋል፡፡ ይህን ተከትሎም ከሀምሌ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ቀናት ጀምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ የነበረ ሲሆን አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት መራዘሙ አይዘነጋም፡፡ የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊና የኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በዚህ ጦርነት ዙሪያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በክልሉ እየተካሄደ…
Read More
አፍሪካ ህብረት በፕሪቶሪያ የተፈረመው የኢትዮጵያን የሰላም ስምምነት መገምገም ጀመረ

አፍሪካ ህብረት በፕሪቶሪያ የተፈረመው የኢትዮጵያን የሰላም ስምምነት መገምገም ጀመረ

በዚህ ግምገማ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት፣ ህወሃት፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ጦርነቱ መቆሙ ይታወሳል፡፡ ይህ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ያለፈው ሲሆን በስምምነቱ መሰረት ያልተፈጸሙ ጉዳዮች እንዳሉ በሁለቱም ወገኖች ሲነሳ ቆይቷል፡፡ አፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተደረሰውን የፕሪቶሪያ የተኩስ ማቆም ስምምነት አፈፃፀም ስትራቴጂካዊ ግምገማ እያካሄደ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አድርገዋል። የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገፃቸው ባጋሩት መልእክት የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት…
Read More
ኢትዮጵያ ለታንዛንያ 400 ሜጋዋት ሀይል ለመሸጥ ተስማማች

ኢትዮጵያ ለታንዛንያ 400 ሜጋዋት ሀይል ለመሸጥ ተስማማች

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሳምንት በታንዛንያ ይፋዊ ጉብኝት አድርገው መመለሳቸው ይታወሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዳሬሰላም ቆይታቸው የአቪዬሽን እና ኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ ስምምነት ከፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሁሉ ሐሰን መንግስት ጋር መፈጸማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ተናግረዋል፡፡ ቃል አቀባዩ በሰጡት ሳምንታዊ የዲፕሎማሲ መግለጫ ለይ እንዳሉት ኢትዮጵያ ለታንዛንያ 400 ሜጋዋት ሀይል ለመሸጥ ስምምነት ፈጽማለች ብለዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ኃይል በተያዘው ዓመት ከሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገራት ከተሸጠ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ሶስት ሺህ ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ጎረቤት ሀገራት በመላክ 182 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዷም ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ለጅቡቲ፣…
Read More
ኢትዮጵያን በአፍሪካ የአይሲቲ ውድድር የሚወክሉ ተወዳዳሪዎች ቱኒዝያ ገቡ

ኢትዮጵያን በአፍሪካ የአይሲቲ ውድድር የሚወክሉ ተወዳዳሪዎች ቱኒዝያ ገቡ

ዘጠኝ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በ8ኛው የሁዋዌ ክፍለ አህጉራዊ የአይሲቲ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው ለመወዳደር ቱኒዚያ ገብተዋል፡፡ በየዓመቱ የሚካሄደው የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ8ኛ ጊዜና በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ6ኛ ጊዜ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተካሄ ይገኛል፡፡ የአገር አቀፍ ማጣሪያና ማጠቃለያ ውድድር ከተካሄደ በኋላ ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አገራቸውን ወክለው በቱኒዚያ በሚካሄደው 8ኛው የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር 2023-2024 ክፈለ አህጉራዊ የፍፃሜ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ቱኒዚያ ይገኛሉ። በውድድሩ ከዘጠኝ አገሮች ከተውጣጡ 90 ተማሪዎች ጋር የሚወዳደሩ ሲሆን እነዚህም አገራት ኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ካሜሩን፣  ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ እና ሞሮኮ ናቸው። ለዚህ አመት ውድድር ከ1,000 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን 280 ተማሪዎች ካሉበት ሆነው…
Read More
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ስራዎች ብቻ ቀርተውታል ተባለ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ስራዎች ብቻ ቀርተውታል ተባለ

ከ13 ዓመት በፊት የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 95 በመቶ መድረሱን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የግድቡ አጠቃላይ የሲቪል ስራው ግንባታ የደረሰበት ደረጃ 98 ነጥብ 9 በመቶ ተጠናቋል የተባለ ሲሆን የኤሌክትሮ መካኒካ ስራው ደውም በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ከአፍሪካ ግዙፉ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴው ግድብ በአሁኑ ወቅት በሁለት ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት በማመንጨት ላይ ይገኛል፡፡ የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም የግድቡ ግንባታ የተጀመረበትን 13ኛ ዓመት አስመልክቶ እንደተናገሩት አሁን ላይ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተመረተ ያለው ኤሌትሪክ ኃይል በ2 ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት መሆኑን ያነሱ…
Read More
ጦርነት እና የማህበራዊ መረዳጃ ተቋማት ስብራት በትግራይ

ጦርነት እና የማህበራዊ መረዳጃ ተቋማት ስብራት በትግራይ

በሀገራችን ኢትዮጵያ ተሰባስቦ ተረዳድዶና ተደጋግፎ መኖር በአጠቃላይ ማህበራዊ ሕይወት አንዱ የሕይወት ዑደት ነው።  ታዲያ ይህ የመረዳዳት ሒደት ደስታን ሐዘንን እንዲሁም የጤና እክልን መሠረት በማድረግ የሚከወን ነው በተለይም እድር እና እቁብን እንደ ምሳሌ ብንወስድ ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ የሚባሉ እና ማህበረሰቡ ጠብቆና አክብሮ የያዛቸው መረዳጃ እና መደጋገፊያ ሕብረቶችናቸው። ታዲያ እነዚህ ሕብረቶች በአንድም በሌላም መልኩ እክል ሲገጥማቸው አሊያም የመፍረስ አደጋ ሲጋረጥባቸው ለመታደግ ጊዜ የሚፈጅ እና አስቸጋሪ ይሆናል። በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ከዛም በፊት በነበረው የኮሮና ወረርሺኝ እንዲህ ያሉ መረዳጃ ማህበራትን ለማጥፋት አሊያም ለማቀዝቀዝ ዋነኛ ምክንያቶች ሆነዋል። በመቀሌ ከተማ የሚገኝ ትልቅ እድር ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ለተኪዳን በነዚህ ሁለት አጋጣሚዎች የተፈጠረውን የእድሩን ከፍተኛ መቀዛቀዝ ሲገልጹ…
Read More
በአማራ ክልል በጦርነት እና ድርቅ ምክንያት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል በጦርነት እና ድርቅ ምክንያት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር እና ድርቅ ምክንያት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል። የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን በክልሉ ያለው የጸጥታ እና ድርቅ ችግሮች በተማሪዎች ምዝገባ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል ብለዋል። ክልሉ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማር ሲገባው ያን ማድረግ አለመቻሉን ኃላፊው ተናግረዋል። ከሁለት ነጥብ 6 ሚሊዮን ያልተመዘገቡ ተማሪዎች መኖራቸውን የገለፁት ኃላፊው ፤ መማር የሚገባቸው ተማሪዎች የትምህርት ዕድል እንዳያገኙ መደረጉን አመልክተዋል። ከ2015 ዓ/ም ሚያዚያ ወር ጀምሮ የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ የሚል ውሳኔ ካሳለፈበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል…
Read More
ኢትዮጵያ በግላስኮው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድርን በአምስተኛነት አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በግላስኮው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድርን በአምስተኛነት አጠናቀቀች

በስኮትላንድ ግላስጎ ሲካሄድ የቆየው የ2024 የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ፍጻሜውን አግኝቷል። ከየካቲት 22 እስክ 24 2016 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው የ19ኛው የዓለም የቤት ዉስጥ ሻምፒዮና ከ130 በላይ ሀገራት  የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶቸ  መሳተፋቸው ተነግሯል። ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር  በሴትና በወንድ  በአጠቃላይ  በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች መሳተፏን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በሻምፒዮናው በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ የወርቅ፣ በሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ የብር እንዲሁም በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች ሆነዋል። በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ  ሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር…
Read More
በባህር ዳር ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከባድ ጦርነት መከሰቱ ተገለጸ፡፡

በባህር ዳር ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከባድ ጦርነት መከሰቱ ተገለጸ፡፡

በአማራ ክልል መዲና ባህርዳር ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከባድ ተኩስ ሲካሄድ እንደነበር ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ ለደህንነታቸው የሰጉ እና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የባህርዳር ከተማ ነዋሪ እንዳሉን ከሆነ ከዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ የተኩስ ድምጽ መስማታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ነዋሪው አክለውም በፍርሃት ቤት ውስጥ በራቸውን ዘግተው ቤተሰባቸውን ይዘው መቀመጣቸውን የነገሩን እኝህ ነዋሪ በተለይም እስከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ መካሄዱንም ነግረውናል፡፡ ውጊው በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል መካሄዱን እርግጠኛ ነኝ የሚሉን እኝህ ነዋሪ ንጹሃን ከቤታቸው ባለሙውጣታቸው የከፋ ጉዳት እንዳላስተናገዱም አክለዋል፡፡ አሁን ላይ በተለይም ከምሳ ሰዓት ጀምሮ የውጊያ ድምጽ እየሰሙ እንዳልሆነ አንቡላንሶች በመንገዶች ላይ ሲመላለሱ መመልከታቸውንም ነግረውናል፡፡ ሌላኛው በባህር ዳር መሀል ከተማ…
Read More
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአራት ክልሎች ምርጫ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአራት ክልሎች ምርጫ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6 ኛውን ዙር ቀሪና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድባቸው አራት ክልሎች ምርጫ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡ ምርጫ የሚካሄደው በጸጥታ እና በሌሎች ምክንያቶች ምርጫ ያልተካሄደባቸው አካባቢዎች ነው የተባለ ሲሆን የቤንሻንጉል ጉምዝ፤ አፋር፤ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 29 የምርጫ ክልሎች ውስጥ እንደሆነም ቦርዱ አስታውቋል፡፡ በዚህ ምርጫ ፕሮግራም ለዘጠኝ የተወካዮች ምክር ቤትና ለሃያ ስድስት የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ለማካሄድ እንደታቀደም ተገልጿል፡፡ ቦርዱ ባወጣው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ መሰረትም የእጩዎች ምዝገባ ከሚያዝያ 7 እስከ ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ/ም ይካሄዳል የተባለ ሲሆን የምረጡኝ ቅስቀሳ ደግሞ ከሚያዚያ 7 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ይካሄዳል፡፡ እንዲሁም የመራጮች ምዝገባ ደግሞ ከሚያዝያ 7 እስከ…
Read More