01
Sep
በደቡብ አሜሪካዋ ፔሩ ሊማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ትናንት ጠናቋል፡፡ በዚህ የአትሌቲክ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡ ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን በ6 ወርቅ፣ 2 ብር እና 2 ነሐስ በአጠቃላይ 10 ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችሏል። በዚህ ኢትዮጵያ ከዓለም አሜሪካን በመከተል 2ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ያጠናቀቀች ሲሆን፤ ውድድሩን 1ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀች አሜሪካ በ8 ወርቅ፣ 4 ብር እና 4 ነሃስ በድምሩ 16 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች በአትሌት መዲና ኢሳ በ5000 ሜትር፣ በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ በ3000 ሜትር መሰናክል በአትሌት ጀነራል ብርሃኑ በ800 ሜትር፣ በአትሌት…