Peru

ኢትዮጵያ በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር አራት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

ኢትዮጵያ በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር አራት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በደቡብ አሜሪካዋ ፔሩ ሊማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ትናንት ጠናቋል፡፡ በዚህ የአትሌቲክ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡ ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን በ6 ወርቅ፣ 2 ብር እና 2 ነሐስ በአጠቃላይ 10 ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችሏል። በዚህ ኢትዮጵያ ከዓለም አሜሪካን በመከተል 2ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ያጠናቀቀች ሲሆን፤ ውድድሩን 1ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀች አሜሪካ በ8 ወርቅ፣ 4 ብር እና 4 ነሃስ በድምሩ 16 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች በአትሌት መዲና ኢሳ በ5000 ሜትር፣ በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ በ3000 ሜትር መሰናክል በአትሌት ጀነራል ብርሃኑ በ800 ሜትር፣ በአትሌት…
Read More
መዲና ኢሳ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈች

መዲና ኢሳ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸነፈች

የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ትናንት በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ፔሩ ተጀምሯል፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ላይ እየተሳተፉ ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችን ከቀናት በፊት ወደ ሊማ ልካለች፡፡ እስካሁን በሁለቱም ጾታዎች የ5 ሸህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን በሁለቱም ጾታ ሜዳሊያ ውስጥ ገብተዋል፡፡ በ5000 ሜትር የሴቶች የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው አሸንፈዋል፡፡ አትሌት መዲና ኢሳ ውድድሩን በ14 ደቂቃ 39 ሰከንድ 71 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። አትሌቷ ውድድሯን ያጠናቀቀችው በገንዘቤ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ28 ሰከንዶች በማሻሻል ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት በተጠናቀቀው የፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ ሰባተኛ ደረጃን ይዛ…
Read More