ዜና

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ማደጉ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ማደጉ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከባንኮች የውጭ ንግድ ግብይት ብቻ በየወሩ 500 ሚሊዮን ዶላር እያገኘች እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ካሳለፍነው ሐምሌ ወር ጀምሮ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲመራ ማድረጓ ይታወሳል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከወጪ ንግድ ብቻ በወር በአማካይ 500 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡ ዋና ገዢው አክለውም የባንክ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፊት ከነበረበት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ወደ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ማደጉንም ገልጸዋል፡፡ አቶ ማሞ አክለውም ከኹለት ሳምንት በፊት በባንኮች መካከል በተጀመረው የእርስ በርስ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግብይት እንደተካሄደም ተናግረዋል። የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገራት…
Read More
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ታገዱ፡፡

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ታገዱ፡፡

የአለም አትሌቲክስ እና ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአበረታች ቅመምች ህግ ጥሰት በፈፀሙ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉ ተገልጿል። የቅጣት ውሳኔው ከተላለፈባቸው አትሌቶች መካከል አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ ፣ አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን እና አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ ሲሆኑ የአበረታች ቅመሞች ህግ ጥሰት መፈጸማቸው ተረጋግጧል ተብሏል። ጥሰቱን ተከትሎም አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ የካቲት 2015 ዓ.ም በተካሄደው ምርመራ ኢፒኦ የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ በዚህም መሰረት አትሌት ሳሙኤል አባተ ለ2 ዓመታት ማለትም እስከ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ድረስ በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፍ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን በተደረገላት የአትሌት ባይሎጂካል ፖስፖርት (ABP) ምርመራ አበረታች ቅመም መጠቀሟ የተረጋገጠባት ሌላኛዋ ኢትዮጵያ አትሌት ስትሆን…
Read More
አዲሱ የኢትዮጵያ ሚዲያ ህግ ማሻሻያ ከሚዲያ እና ህግ ባለሙያዎች ማህበራት ተቃውሞ ገጠመው

አዲሱ የኢትዮጵያ ሚዲያ ህግ ማሻሻያ ከሚዲያ እና ህግ ባለሙያዎች ማህበራት ተቃውሞ ገጠመው

የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ሁሉን ያሳተፈ ውይይት በአስቸኳይ እንዲደረግበት  ተጠይቋል፡፡ ከአንድ ወር በፊት በስራ ላይ ያለው የሚዲያ ህግ እንዲሻሻል ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ በቂ የባለድርሻ አካላት ውይይት ሳይደረግበት ወደ ቋሚ ኮሚቴ መመራቱ ትክክል እንዳልሆነ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የጋዜጠኞች፣ ህግ እና ሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ማህበራት ተችተዋል፡፡ 14 የጋዜጠኞች፣ ህግ እና ሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ማህበራት በጋራ ባወጡት መግለጫ የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የሕዝብንም ሆነ የባለድርሻ አካላትን ድምፅ በተገቢ ያላካተተ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡ የጋዜጠኞች ማህበራት እና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013ን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ…
Read More
ኢትዮጵያ የአትክልት ምርቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ገበያ አቀረበች

ኢትዮጵያ የአትክልት ምርቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ገበያ አቀረበች

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአትክልት ምርቶች በመርከብ ለአውሮፓ ገበያ ተልከዋል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአትክልት ምርቶች በመርከብ ተጓጉዘው ለአውሮፓ ገበያ መላካቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ኢትዮ ቬጅ ፍሩ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በተሰኘ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራች ድርጅት በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሹገር ስናብ እና ማንጄቱት የተባሉ የአትክልት ምርቶችን በመርከብ በማጓጓዝ ወደ ኔዘርላንድ መላኩ ተጠቅሷል። በዚህም 12 ቶን ሹገር ስናብ እና ማንጄቱት የአትክልት ምርቶችን ዘመናዊ የማቀዝቀዣ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ኮንቴነር በመጠቀም ጅቡቲ ወደብ ከደረሰ በኃላ በመርከብ መላኩ ተገልጿል። የአትክልት ምርቱ ከቆቃ ተነስቶ በመርከብ ተጓጉዞ በ23 ቀናት ውስጥ ኔዘርላድ እንደሚደርስም ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የአውሮፓ ሀገራት የኢትዮጵያ ግብርና ምርቶች ዋነኛ መዳረሻ ሲሆን ከጠቅላላው…
Read More
ጎግል ፕሌይ ኢትዮጵያዊን ባለሙያዎችን መቀበል ጀመረ

ጎግል ፕሌይ ኢትዮጵያዊን ባለሙያዎችን መቀበል ጀመረ

የጎግል ፕሌይ አልሚዎች ምዝገባ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል ጀምሯል። ኢትዮጵያውያን አልሚዎች በጎግል ፕሌይ ላይ ተቀባይነት ማግኘተቻው የተለያዩ መተግበሪያዎችን እያለሙ ዓለም አቀፍ ደንበኞችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጎግል ኩባንያ ጋር ያደረጋቸው ተደጋጋሚ ጥረቶች ለዚህ እንዳበቃቸው ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያዊያን የአይሲቲ ባለሙያዎች የGoogle Playን አለምአቀፍ ታዳሚዎች በቀጥታ በማስገኘት መተግበሪያዎቻቸው ሰፊ እይታን እንዲያገኝ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችላልም ተብሏል፡፡ ይህ ምዕራፍ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ባለቤቶች መተግበሪያዎቻቸውን በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ ዲጂታል መድረኮች ላይ እንዲያትሙ አዲስ እድሎችን የሚከፍት እንደሆነም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ዶ/ር እንዳሉት መንግስት የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመገንባት በርካታ ተነሳሽነቶችን በመተግበር እየሰራ መሆኑን ገልጸው ይህ አዲስ ጅማሮ…
Read More
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ሶስት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ተስማ

የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ሶስት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ተስማ

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዎች ለሰዎች ፋውዴሽን ጋር ሦስት ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል። የስምምነት ሰንዱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰባስቲያን ብራንዲስ ተፈራርመዋል። በመግባቢያ ስምምነቱም ሰዎች ለሰዎች ፋውንዴሽን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለመገንባት ካቀዳቸው 13 ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ሦስቱን የሚገነባ መሆኑ ተጠቅሷል። የልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ የሚካሄድው በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው አዲስ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ዲዛይን መሰረት ነው ተብሏል፡፡ የአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ሙሉ የግንባታ ወጪን በመሸፈን እንዲሁም ለመማር ማስተማር ሥራው…
Read More
የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፈተ

የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፈተ

ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የፋሽን፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችዎቸን በአንድ ጣራ ስር የሚያሰባስበው የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡ በአፍሪካ አህጉር ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን የሆነው "10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት(10th AFRICA SOURCING AND FASHION WEEK  ASFW ) በአዲስ አበባ  ስካይ ላይት ሆቴል ከዛሬ ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል። የፋሽን ሳምንቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስት አቶ መላኩ አለበል፣ ክብርት ሌንሳ መኮንን፣ በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ እና ሌሎች በርካታ አንግዶች ከፍተውታል፡፡ ዝግጅቱ አለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ፈጣሪዎችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰብሰብ እስካሁን  ከተደረጉት ዝግጅቶች ሁሉ ትልቁ  ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የአፍሪካ ሶርሲንግና…
Read More
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለዶናልድ ትራምፕ እነኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለዶናልድ ትራምፕ እነኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እየመሩ ገኛሉ፡፡ ትራምፕ እስካሁን በተረጋገጡ የወኪል መራጮች ምርጫ አማካኝነት 267 በ224 ድምጽ እየመሩ ይገኛሉ፡፡ አስቀድሞ 270 የወኪል መራጮችን ድምጽ ያገኘ እጩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይሆናል በሚለው ህግ መሰረት ዶናልድ ትራምፕ በይፋ ማሸነፋቸውን ለማወጅ ሶስት ድምጽ ብቻ መቅረቱን ተከትሎ በርካታ የዓለማችን ሀገራት አስቀድመው እንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን እያስተላለፉ ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከልም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አንዱ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ስላሸነፉ እንኳን ደስ አለዎት፣ ወደ መሪነት እንኳን ድጋሚ መጡ አብረን እንደምንሰራ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ለዶናልድ ትራምፕ እና ባለቤታቸው እንኳን ወደ…
Read More
የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ባንኮች ወደ የኢትዮጵያ ለመግባት እያሰቡ ነው ተባለ

የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ባንኮች ወደ የኢትዮጵያ ለመግባት እያሰቡ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ እስካሁን በሯን ለውጭ ባንኮች ዝግ አድርጋ የቆየች ሲሆን አሁን ላይ የፖሊሲ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ የውጭ ሀገራት ባንኮች እንዲገቡ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በፊት መግለጹ ይታወሳል፡፡ ለዚህም ሲባል የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከአንድ ዓመት በፊት የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ ለመግባት ከስድስት ወራት በፊት አመልክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የሞሮኮ፣ የኬንያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ባንኮች በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋ፡፡ ዋና ገዢው አክለውም የውጭ ሀገራት ባንኮች በኢትዮጵያ እንዲሰሩ የሚፈቅደው ህግ በቀጣዮቹ ሳምንታት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚጸድቅ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለማግኘት የሚፈልጉ…
Read More
አሜሪካ በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት አሳስቦኛል አለች

አሜሪካ በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት አሳስቦኛል አለች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገልጿል። “በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶች እልባት እንዲያገኙ የፖለቲካ ውይይት ወሳኝነት አለው” ሲሉ አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር አብይ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ወቅት መናገራቸው የመስሪያ ቤታቸው መግለጫ አመላክቷል። አሜሪካ “በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ያሳስባታል” ሲሉ መናገራቸውን በመግለጫው ላይ ተገልጿል። አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በስልክ ያወሩት በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ዙሪያ እንደነበር ጸ/ቤታቸው ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አንቶኒ ብሊንከን “ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲደረግ ለምታደርገው ጥረት ሀገራቸው እገዛ ለማድረግ ዝግጁ ናት” ሲሉ መናገራቸውን መግለጫው ጠቁሟል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር…
Read More