ዜና

በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት ባለስልጣንን ጨምሮ ከ60 በላይ ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት ባለስልጣንን ጨምሮ ከ60 በላይ ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች ውስጥ በመንግስት የጸጽታ ሀይሎች እና የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ በመካሄድ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል ውጊያ ከሚካሄድባቸው ወረዳዎች መካከል አንዱ በሆነው ደራ ወረዳ በትናንትናው ዕለት  ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ባለስልጣንን ጨምሮ ንጹሃን ዜጎች ተገድለዋል፡፡ ከተገደሉት መካከል የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩን አንዱ ሲሆኑ ከአስተዳዳሪው በተጨማሪም የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ንጹሃን ዜጎችም ገኙበታል ተብሏል፡፡ የአመራሩ ግድያ የተፈጸመው አመራሩና በርካታ የጸጥታ ሃይሎች መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ሃይል ወደሚንቀሳቀስበት አካባቢ ሲያመሩ ነው ተብሏል። በደራ ወረዳ ገንዶ መስቀል አካባቢ ላለፉት ሶስት ሳምንታት የመከላከያ ሰራዊትን፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን (ወይም መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለውን) እና የፋኖ…
Read More
ኢትዮጵያ ሞቶ የተገኘ አስከሬንን ለምርምር መጠቀም እንዲቻል የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ ሞቶ የተገኘ አስከሬንን ለምርምር መጠቀም እንዲቻል የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

ከሁለት ሳምንት በፊት የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ይህ ረቂቅ ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የአስከሬን አያያዝ እና ዝውውር ጉዳይ አንዱ ሲሆን በርካታ ጉዳዮችን ደንግጓል፡፡ ከነዚህ መካከልም በህግ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ካልፈቀደ በስተቀር የሰው አካል ክፍልን፣ አስክሬንን ወይም አጽምን ወደ ሐገር ውስጥ ማስገባት ወይም ከሐገር ማስወጣትን ይከለክላል፡፡ እንዲሁም አስከሬንን ለማስተማሪያነት ወይም ለምርምር ማዘጋጀት የሚችለው አግባብነት ባለው አካል የተመረጠ የጤና ተቋም ነው እንደሆነም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተጠቅሷል፡፡ ማንኛውም አስክሬንን ለማስተማሪያነት ወይም ለምርምር እንዲያዘጋጅ የተመረጠ ተቋም ያዘጋጀውን አስክሬን ከሌላ የማስተማሪያ እና የምርምር ተቋም ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሰረት አስክሬንን ለማስተማሪያነት እና ለምርምር ተግባር እንዲውልም ይፈቅዳል፡፡ አስከሬንን…
Read More
ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ዳታ ማይኒንግ ኩባያዎች 27 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ዳታ ማይኒንግ ኩባያዎች 27 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ለጎረቤት አገራት ከሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ከ31 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቱን አስታወቀ። ተቋሙ ለጅቡቲ ከሸጠው ከ169 ሺሕ 710 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል፣ 10 ሚሊዮን 379 ዶላር እና ለኬንያ ከሸጠው ከ314 ሺሕ 931 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል ከ20 ሚሊዮን 470 ሺሕ ዶላር ማግኘቱ ተገልጿል። በተመሳሳይ፣ ተቋሙ ለሱዳን ካቀረበው ከ13 ሺሕ 185 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ከ659 ሺሕ በላይ ዶላር ያገኘ ሲኾን፣ በሱዳኑ ጦርነት ሳቢያ ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ለአገሪቱ ለማቅረብ ካቀደው ኃይል ውስጥ ያቀረበው 15 በመቶውን ብቻ እንደኾነ ተገልጧል። ኢትዮጵያ ውስጥ በዲጂታል መረጃ ማቀነባበር ከተሠማሩ የውጭ ኩባንያዎች በሩብ ዓመቱ ውስጥ ከተሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ደግሞ፣…
Read More
እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ያሉ ተማሪዎችን በውጤታቸው ደረጃ መስጠትን ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ያሉ ተማሪዎችን በውጤታቸው ደረጃ መስጠትን ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

በሳሙኤል አባተ ኢትዮጵያ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅታለች፡፡ ይህ ረቂ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ በትናንትናው ዕለት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም ይህን ረቂቅ አዋጅ ተጨማሪ ውይይቶች እና ሌሎች ግብዓቶች እንዲታከሉበት በሚል ለዝርዝር እይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ እንደሚለው ከሆነ ተማሪዎች ስለ ሚማሯቸው ቋንቋዎች፣ ስርዓት ትምህርት ዝግጅት፣ መምህራን ቅጥር፣ ተማሪዎች ምዘና፣ ትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ መንገዶች እና ሌሎችንም ጉዳዮች ይዟል፡፡ ቋንቋዎችን አስመልክቶ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተቀመጠው የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ ብሏል፡፡…
Read More
የአቦል አዳዲስ ይዘቶች ማስተዋወቂያ እና የአፋፍ ቴሌኖቬላ ማጠናቀቂያ ልዩ ዝግጅት ተካሄደ

የአቦል አዳዲስ ይዘቶች ማስተዋወቂያ እና የአፋፍ ቴሌኖቬላ ማጠናቀቂያ ልዩ ዝግጅት ተካሄደ

ሕንድ ለ20 የፊልም ሙያተኞች የስኮላርሽፕ እድል ሰጥታለች “የአቦል አዳዲስ ይዘቶች ማስተዋወቂያና የአፋፍ ቴሌኖቬላ ማጠናቀቂያ” ልዩ በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት አዳራሽ (ወመዘክር) ተካሂዷል፡፡ በዚህ መድረክ ላይ ታዋቂ የፊልም ባለሙያዎች፣ ተወናዮች፣ የመንግስት ተቋማት ሃለፊዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልመህዲ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር "ዲኤስቲቪ በኢትዮጵያ የፊልም ጥበብ እንዲጎለብት በፋይናንስና በስርጭት እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው። በርካቶች የፊልም ጥበብ ባለሙያዎች ይህንን በመጠቀም እየተንቀሳቀሱ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ለዚህ ማሳያ የሆነው " አፋፍ ተከታታይ ድራማ በፕሮዳክሽን ጥራትም በይዘትም ምሳሌ በሚሆን መልኩ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ነበር" ብለዋል። በስኬት በመጠናቀቁም የይዘት ባለቤቱን ዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥንና አዘጋጁን ሚካኤል…
Read More
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሹመት ተቃውሞ ገጠመው

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሹመት ተቃውሞ ገጠመው

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የአምስት ሚንስትሮችን ሹመት ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውሳኔ አሳልፏል። ለምክር ቤቱ ከቀረቡ አጀንዳዎች መካከል የአምስት ሚንስትሮች ሹመት አንዱ ሲሆን የምክር ቤት አባላት እና የመንግስት ተጠሪ ክርክር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሁለት ሳምንታት በፊት የሾሟቸው አምስት ሚንስትሮች በዛሬው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የቀረበ ሲሆን የምክር ቤት አባላት በሹመቱ ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከልም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተደርገው የተሾሙት እና ስራ የጀመሩት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) አንዱ ነበር። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ወክለው የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጥያቄ ካነሱት መካከል አንዱ ነበሩ። ሹመቱን አስመልክቶ ካነሱት ጥያቄ መካከልም "የፍትህ…
Read More
ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ተፋናቃዮችን ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችል ህግ እንደሌላት ተገለጸ

ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ተፋናቃዮችን ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችል ህግ እንደሌላት ተገለጸ

የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው መጠለያዎች ታጣቂዎች ሰርገው እየገቡ ጥቃት መፈጸማቸው ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ ለአንድ ዓመት ያደረገውን ሪፖርት ፋ አድርጓል፡፡ ተቋሙ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሦስተኛውን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ባለ 52 ገጽ ሪፖርት  ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ሪፖርት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎችን እና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል። ኢሰመኮ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሐረሪ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሊ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልሎች በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋ መንስኤዎች የተፈናቀሉ ከ333 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ ተመላሾችን እና ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ የተደረጉ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል እና…
Read More
የአማራ ዳኞች ማህበር የታሰሩ አባላቱ እንዲፈቱ ጠየቀ

የአማራ ዳኞች ማህበር የታሰሩ አባላቱ እንዲፈቱ ጠየቀ

የፌደራል መንግስት ክልል የክልል ልዩ ሀይሎችን ዳግም አደራጃለሁ በሚል ውሳኔ ካሳለፈበት ሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች አማካኝነት ጦርነት ተቀስቅሷል፡፡ በክልሉ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ አዋጅ ከ10 ወራት በኋላ ያልተራዘመ ቢሆንም አሁንም በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ጦርነቶች እየተካሄዱ ናቸው፡፡ ከጦርነቱ ባለፈም በክልሉ ንጹሃን ዜጎች በጅምላ እየታሰሩ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም የአማራ ዳኞች ማህበር እና ጤና ባለሙያዎች ማህበር አባላቶቻቸው ለተለያዩ ጉዳቶች መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር እንዳለው በክልሉ ያለው የደህንነት ችግር ዳኞች በነጻነት ስራቸውን እንዳይሰሩ እክል መፍጠሩን ገልጾ ባለፉት ቀናት ውስጥም 13 ዳኞች ታስረዋል፡፡ ከታሰሩት ውስጥ አራት ዳኞች ከእስር መለቀቃቸውን የተናገረው ማህበሩ ቀሪ እና በእስር…
Read More
ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች 

ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች 

በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራት ከወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) አፈጻጸምን ከላኪዎች ጋር መገምገማቸውን አስታውቀዋል። አፈጻጸሙ በምርት ጭማሪም ሆነ በውጭ ምንዛሪ ዕድገት ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን አመላክተዋል። ይህም ከዕቅዱ 132 በመቶ መሳካቱንና ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ አለው ተብሏል። በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን በማላቅ ኢኮኖሚው የሚፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ ከዘርፉ ተዋናዮች እና ከላኪዎች ጋር የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም አመላክተዋል። ይህ በዚህ…
Read More
የአሜሪካው ቢትኮይን ክሪፕቶከረንሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ መሰማራቱን ገለጸ

የአሜሪካው ቢትኮይን ክሪፕቶከረንሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ መሰማራቱን ገለጸ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምናባዊ ገንዘብ ወይም የክሪፕቶከረንሲ ግብይት ፍላጎት እየጨመረ ሲሆን በኢትዮጵያም አጀንዳ ከሆነ አምስት ዓመት ሆኖታል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የትኛውንም ክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት እንዳልፈቀደ እና ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ ሰዎችም በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስታውቆ ነበር፡፡ ካሳለፍነው ዓመት ጀምሮ በኢትዮጵያ የቢትኮይን ግብይት መፈጸም የሚያስችሉ መሰረተ ልማት ግንባታ የሚያደርጉ ኩባያዎች ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኢትዮጵያ አሁንም የክሪፕቶከረንሲ ግብይት እንዲደረግ ያልፈቀደች ሲሆን የዳታ ማዕከል ግንባታዎች እንዲካሄዱ ግን ስምምነቶችን በመፈራረም ላይ ነች፡፡ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የዎልስትሪቱ ቢትፉፉ የተሰኘው የክሪፕቶከረንሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ መሰማራት የሚያስችለውን ሂደት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው የክሪፕቶከረንሲ ግብይት ማካሄድ የሚያስችል የ80 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ሀይል መሰረት ልማት መግዛቱን ገልጿል፡፡ ቢትፉፉ የተሰኘው ይህ…
Read More