ዜና

ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅም እንዳላት ገለጸች

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ በይፋ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በ2029 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ የማዘጋጀት አቅም አላት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ጠይቀዋል፡፡ የፊፋ፣ ካፍ እና ሌሎች የእግር ኳስ አመራሮች በአዲስ አበባ በተካሄደው የካፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ለዚህ ጉባኤ ተሳታፊዎች ላይ በተዘጋጀ እራት ግብዣ ላይ ንግግር ደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ የ2029 አፍሪካ ዋንጫን እንድታዘጋጅ በይፋ ጠይቀዋል። የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሙትሴፔ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል  ምስጋና አቅርበው፣ የኢትዮጵያውያን ባህል፣እሴትና እንግዳ ተቀባይነት ኢትዮጵያ  ቤታችን እንደሆነች እንዲሰማን አድርጎናል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የ2029ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ ከኮሚቴው…
Read More
የራይድ ታክሲ ተጠቃሚ በመምሰል ሾፌሮችን ሲገድሉ የነበሩ አራት ግለሰቦች በሞት ተቀጡ

የራይድ ታክሲ ተጠቃሚ በመምሰል ሾፌሮችን ሲገድሉ የነበሩ አራት ግለሰቦች በሞት ተቀጡ

የታክሲ ኮንትራት በመጥራት ሹፌሮችን በመግደል ተሽከርካሪ ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላለፈባቸው በተለያዩ ጊዜያት አሽከርካሪዎችን  ራቅ ወዳለ ስፍራ እየወሰዱ በመግደል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር  ስር ውለው በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል። በአዲስ አበባ ገላን ክፍለ ከተማ፣ በሳሪስ እንዲሁም በቢሾፍቱ መኖሪያቸውን ያደረጉት ቴዎድሮስ ብርሃኔ እና  እዩኤል ቴዎድሮስ እንዲሁም በሌላ በኩል ተፈሪ ተስፋዬ እና ዩሃንስ አረፋ  የተባሉት ግለሰቦች  ከአዲስ አበባ ቢሾፍቱ በመመላለስ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር  የሸገር ከተማ አስተዳደር  ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ዓቃቢ ህግ አቶ ሚዴቅሳ አጋሩ  ተናግረዋል። አራት ግለሰቦች ከግል ተበዳዮች በኮንትራት በመውሰድ ከዋናው መንገድ ውጪ በማስውጣት የአሽከርካሪዎቹን ህይወት በማጣፋት ተሽከርካሪዎቹን ይዞ በመሰወር  ለተለያዩ ጋራዦች እና  ግለሰቦች በመሸጥ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር ተገልጿል። ቴዎድሮስ እና…
Read More
ኦብነግ ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ ራሱን አገለለ

ኦብነግ ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ ራሱን አገለለ

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ እራሱን ማግለሉን አስታወቀ  የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ድርጅት አሳታፊነትና ግልጸኝነት ስላላየሁበት ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳታፊነት እራሴን አግልያለሁ ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በሱማሌ ክልል የገዢው ፓርቲ መዋቅር ተሳታፊዎችን የሚለይበትና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድምጽ የሚያፍንበት ህገ-ወጥ  አሰራር መዘርጋቱን የሚገልጸው ፓርቲው በዚህ ሂደት ውስጥ በምክክር መሳተፍ ረብ የለሽ ነው ሲልም ገልጿል፡፡ ይህ አግላይ አሰራር አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተቋቋመበትን አላማ የሚጥስ ነው ሲልም በምክክር ኮሚሽኑ ሂደት ላይ ጥያቄ አንስቷል፡፡ ፓርቲው ከሱማሌ ክልል ውጪ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳሱ የታጠቁ ሃይሎች ባልተሳተፉበት ሁኔታ እንዴት የምክክር ሂደቱ ሊሳካ ይችላል ሲልም በጥያቄ መልስ አንስቷል፡፡ በቀጣይም ሁሉን አቀፍ የድርድር መድረክ እስካልተዘጋጀ…
Read More
መዳን የማይችሉ ሰዎችን ህይወት ማቋረጥ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ለፓርላማ ቀረበ

መዳን የማይችሉ ሰዎችን ህይወት ማቋረጥ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ለፓርላማ ቀረበ

መዳን የማይችሉ ሰዎችን ህይወት ማቋረጥ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት ባሳለፍነው ሳምንት የቀረበው ይህ ረቂቅ አዋጅ "የጤና አገልግሎት አስተዳደር አዋጅ" ተብሎ ቀርቧል፡፡ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በርካታ ከጤና ጋር የተያያዙ ስርዓቶች የቀረቡ ሲሆን በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ባለትዳሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ የህክምና አገልግሎት ስለሚያገኙበት መንገድ ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አተነፋፈሳቸው በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ የሚደነግግ ረቂቅ ህግም ለምክር ቤቱ ቀርቦለታል፡፡ የዚህ ረቂቅ ህግ አላማም የሃገሪቱን እድገት ለማሳለጥና የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል በሚደረግ ጥረት የልማቱ አንቀሳቃሽ የሆነውን ሕዝብ ጤንነት በተሟላ ሁኔታ መጠበቅ እንደሆነ ተጠቅሷል። በዚህ ረቂቅ ህግ መሰረት በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን…
Read More
በኢትዮጵያ ከሞቱ ሰዎች ኩላሊት እንዲለገስ የሚፈቅድ ህግ እንዲዘጋጅ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ ከሞቱ ሰዎች ኩላሊት እንዲለገስ የሚፈቅድ ህግ እንዲዘጋጅ ተጠየቀ

ኩላሊት ከሞተ ሰው እንዲወሰድ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ከስድስት ዓመት በፊት የተዘጋጀ ቢሆንም እስካሁን መልስ እንዳላገኘ የኩላሊት ህመምተኞች ማህበር ተናግሯል፡፡ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ የኩላሊት ልገሳን ከቤተሰብ ውጭ እንዲለገስ የማይፈቅደው የኢትዮጵያ የጤና ህግ  እንዲሻሻል ቢጠየቅም መልስ አለማግኘቱ ችግር እንደሆነ ተነግሯል። በቅርቡ በተወካዮች ምክር ቤት የጤና ህጎች ረቂቅ አዋጅ መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን ስለ ኩላሊት ልገሳ የሚያወራው ህግ ግን እስካሁን እንዳልቀረበ  በኩላሊት ተካሚዎች ማህበር በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ኩላሊት ከሞተ ሰው በቀዶ ህክምና ከበጎ ፈቃደኞች እንዲወሰድ የሚረዳ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ላለፉት ስድስት ዓመታት እየተጠየቀ ቢቀጠልም እስካሁን ተግባራዊ መሆን እንዳልተቻለም  አስታውቀዋል። ከቤተሰብ የሚደረገው የልገሳ ሂደትም በለጋሽ…
Read More
ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ የ10 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች

ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ የ10 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች

በኢትዮጵያና በኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የ10 ሚሊዮን ዶላር የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት ተፈርሟል፡፡ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በኮሪያ ሪፐብሊክ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ መካከል የኢትዮጵያ የጥራት አመራር አቅም ማጎልበቻ ፐሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የግብርና እና የተቀናበሩ የግብርና ምርት ውጤቶች ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ላይ ያተኩራል የተባለ ሲሆን ለዚህም ደቡብ ኮሪያ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 10 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ታደርጋለች ተብሏል፡፡ በፊርማ ስነስርዓቱ በኢትዮጵያ የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሚስተር ሃን ዲዩግ ቾ እንደገለፁት የኢትዮጵያና የኮሪያ ሪፐብሊክ ግንኙነት ታረካዊ ነው ያሉ ሲሆን በኮሪያ ጦርነት ወቅት ከ6000 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለኮሪያ ህዝብ ተዋግተው የደም ዋጋ የከፈሉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የፕሮጀክት ስምምነቱ የኮሪያ እና የኢትዮጵያ ወዳጅነትን…
Read More
ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተለያዩ ተቋማት አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል። በዚህም መሰረት ጌዲዮን ጥሞቲዮስ (ዶ/ር) በቅርቡ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ተደርገው በተሾሙት ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በተጨማሪም ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ  ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ ፍትህ ሚኒስትር ተደርገው ከመሾማቸው በፊት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ እንዲሁም የመንግስት ኮሙንኬሽን ምክትል ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱርዝም ሚንስትር ተደርገው መሾማቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፤…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቀረበ

ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቀረበ

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጩን በይፋ አስጀምሯል፡፡ 100 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ሀብት ያለው ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡ አንዱን የድርጅቱን አክስዮን ዋጋ በ300 ብር እንደሚሸጥ ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም አንድ ግለሰብ መግዛት የሚችለው 33 አክስዮን ወይም 9 ሺህ 900 ብር ነው ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮ ቴሌኮም 3 ሺህ 333 አክስዮኖቹን ለሽጭ ያቀረበ ሲሆን 30 ቢሊዮን ብር ከአክስዮን ሽያጭ ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች አክስዮን መግዛት ይችላሉ የተባለ ሲሆን ተቋማት ግን አክሲዮንን መግዛት እንደማይችሉ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡ የአክሲዮን ሽያጩ ከዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃልም…
Read More
የኢትዮጵያ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫን እንዲያጠቡ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫን እንዲያጠቡ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከውጭ ምንዛሪ ግብይት ጋር በተያያዘ ስለሚፈጸሙ ክፍያዎች የማሻሻያ ፖሊሲ ይፋ አድርጓል:: ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በዚህም ባንኮች በየእለቱ በሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ የዋጋ ተመን ላይ በመግዣ እና በመሸጫው መካከል ከ10 በላይ ልዩነት ሲታይበት ቆይቷል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫው፤ አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል። በመሆኑም የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት…
Read More
የኢትዮጵያ ብርቅዬ የዱር እንስሳ የሆነው ዋልያ የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበታል ተባለ

የኢትዮጵያ ብርቅዬ የዱር እንስሳ የሆነው ዋልያ የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበታል ተባለ

በኢትዮጵያ ካሉ የዱር እንስሳት መጠለያዎች ውስጥ አንዱ በሆነው በ ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ከ900 በላይ ዋልያዎች የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ቁጥራቸው ወደ 300 ዝቅ ብሏል፡፡ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ መኖሪያቸውን ያደረጉና ከዚህ ቀደም ቁጥራቸው ከ900 በላይ የነበሩ ዋልያዎች ወደ 306 ዝቅ ማለታቸውን የፓርኩ ፅህፈት ቤት አስታውቋል:: የፓርኩ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ማሩ ቢያድግልኝ እንደተናገሩት በክልሉ በነበረው የፀጥታ ችግር በተሰማው የተኩስ ድምፅ በፓርኩ ውስጥ የነበሩ ብርቅዬ እንስሳቶች በመረበሻቸው በአሁኑ ሰአት ቁጥራቸው ቀንሷል ብለዋል:: አለመረጋጋቱን ተከትሎ በዋና ዋና የዱር እንስሳቶች መናሃሪያ ቦታዎች ላይ የጦር መሳሪያዎች የነበሩ በመሆናቸው በርካታ የዱር እንስሳቶች ከአካባቢዉ መራቃቸውን  የገለፁት ኃላፊው ከእነዚህም መካከል ዋልያዎች ተጠቃሽ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። በሚመለከተው አካል በኩል…
Read More