14
Oct
በኢትዮጵያ ካሉ የዱር እንስሳት መጠለያዎች ውስጥ አንዱ በሆነው በ ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ከ900 በላይ ዋልያዎች የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ቁጥራቸው ወደ 300 ዝቅ ብሏል፡፡ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ መኖሪያቸውን ያደረጉና ከዚህ ቀደም ቁጥራቸው ከ900 በላይ የነበሩ ዋልያዎች ወደ 306 ዝቅ ማለታቸውን የፓርኩ ፅህፈት ቤት አስታውቋል:: የፓርኩ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ማሩ ቢያድግልኝ እንደተናገሩት በክልሉ በነበረው የፀጥታ ችግር በተሰማው የተኩስ ድምፅ በፓርኩ ውስጥ የነበሩ ብርቅዬ እንስሳቶች በመረበሻቸው በአሁኑ ሰአት ቁጥራቸው ቀንሷል ብለዋል:: አለመረጋጋቱን ተከትሎ በዋና ዋና የዱር እንስሳቶች መናሃሪያ ቦታዎች ላይ የጦር መሳሪያዎች የነበሩ በመሆናቸው በርካታ የዱር እንስሳቶች ከአካባቢዉ መራቃቸውን የገለፁት ኃላፊው ከእነዚህም መካከል ዋልያዎች ተጠቃሽ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። በሚመለከተው አካል በኩል…