02
Nov
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች ውስጥ በመንግስት የጸጽታ ሀይሎች እና የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ በመካሄድ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል ውጊያ ከሚካሄድባቸው ወረዳዎች መካከል አንዱ በሆነው ደራ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ባለስልጣንን ጨምሮ ንጹሃን ዜጎች ተገድለዋል፡፡ ከተገደሉት መካከል የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩን አንዱ ሲሆኑ ከአስተዳዳሪው በተጨማሪም የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ንጹሃን ዜጎችም ገኙበታል ተብሏል፡፡ የአመራሩ ግድያ የተፈጸመው አመራሩና በርካታ የጸጥታ ሃይሎች መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ሃይል ወደሚንቀሳቀስበት አካባቢ ሲያመሩ ነው ተብሏል። በደራ ወረዳ ገንዶ መስቀል አካባቢ ላለፉት ሶስት ሳምንታት የመከላከያ ሰራዊትን፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን (ወይም መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለውን) እና የፋኖ…