Coffin

ኢትዮጵያ ሞቶ የተገኘ አስከሬንን ለምርምር መጠቀም እንዲቻል የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ ሞቶ የተገኘ አስከሬንን ለምርምር መጠቀም እንዲቻል የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

ከሁለት ሳምንት በፊት የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ይህ ረቂቅ ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የአስከሬን አያያዝ እና ዝውውር ጉዳይ አንዱ ሲሆን በርካታ ጉዳዮችን ደንግጓል፡፡ ከነዚህ መካከልም በህግ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ካልፈቀደ በስተቀር የሰው አካል ክፍልን፣ አስክሬንን ወይም አጽምን ወደ ሐገር ውስጥ ማስገባት ወይም ከሐገር ማስወጣትን ይከለክላል፡፡ እንዲሁም አስከሬንን ለማስተማሪያነት ወይም ለምርምር ማዘጋጀት የሚችለው አግባብነት ባለው አካል የተመረጠ የጤና ተቋም ነው እንደሆነም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተጠቅሷል፡፡ ማንኛውም አስክሬንን ለማስተማሪያነት ወይም ለምርምር እንዲያዘጋጅ የተመረጠ ተቋም ያዘጋጀውን አስክሬን ከሌላ የማስተማሪያ እና የምርምር ተቋም ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሰረት አስክሬንን ለማስተማሪያነት እና ለምርምር ተግባር እንዲውልም ይፈቅዳል፡፡ አስከሬንን…
Read More