wada

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ታገዱ፡፡

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ታገዱ፡፡

የአለም አትሌቲክስ እና ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአበረታች ቅመምች ህግ ጥሰት በፈፀሙ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉ ተገልጿል። የቅጣት ውሳኔው ከተላለፈባቸው አትሌቶች መካከል አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ ፣ አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን እና አትሌት ህብስት ጥላሁን አስረስ ሲሆኑ የአበረታች ቅመሞች ህግ ጥሰት መፈጸማቸው ተረጋግጧል ተብሏል። ጥሰቱን ተከትሎም አትሌት ሳሙኤል አባተ ዘለቀ የካቲት 2015 ዓ.ም በተካሄደው ምርመራ ኢፒኦ የተባለውን የተከለከለ ንጥረ ነገር መጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡ በዚህም መሰረት አትሌት ሳሙኤል አባተ ለ2 ዓመታት ማለትም እስከ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ድረስ በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፍ ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ አትሌት ፀሐይ ገመቹ በያን በተደረገላት የአትሌት ባይሎጂካል ፖስፖርት (ABP) ምርመራ አበረታች ቅመም መጠቀሟ የተረጋገጠባት ሌላኛዋ ኢትዮጵያ አትሌት ስትሆን…
Read More