አካባቢ ጥበቃ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ስራዎች ብቻ ቀርተውታል ተባለ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ስራዎች ብቻ ቀርተውታል ተባለ

ከ13 ዓመት በፊት የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 95 በመቶ መድረሱን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባት ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የግድቡ አጠቃላይ የሲቪል ስራው ግንባታ የደረሰበት ደረጃ 98 ነጥብ 9 በመቶ ተጠናቋል የተባለ ሲሆን የኤሌክትሮ መካኒካ ስራው ደውም በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ከአፍሪካ ግዙፉ ፕሮጀክት የሆነው የህዳሴው ግድብ በአሁኑ ወቅት በሁለት ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት በማመንጨት ላይ ይገኛል፡፡ የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሃም የግድቡ ግንባታ የተጀመረበትን 13ኛ ዓመት አስመልክቶ እንደተናገሩት አሁን ላይ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተመረተ ያለው ኤሌትሪክ ኃይል በ2 ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት መሆኑን ያነሱ…
Read More
አዲሱ የአውሮፓ ህብረት ሕግ በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች ላይ የሕልውና አደጋ ደቅኗል ተባለ

አዲሱ የአውሮፓ ህብረት ሕግ በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎች ላይ የሕልውና አደጋ ደቅኗል ተባለ

የአውሮፓ ህብረት ከሁለት ሳምንት በፊት ባወጣው አዲስ ህግ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን የሚጎዱ ምርቶችን ወደ ህብረቱ አባል ሀገራት ገበያዎች እንዳይገቡ እና እንዳይሸጡ አደርጋለሁ ብሏል፡፡ የምድርን ሙቀት ለመከላከል እና የደን ምንጣሮን ለመከላከል ይረዳል በሚል የተዘጋጀው ይህ ህግ ከደን ምርቶች ጋር የተያያዙ ምርቶች በአውሮፓ የገበያ እድል እንዳያገኙ መከልከል እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ማበረታታት የህጉ ዋነኛ ዓላማ ነው፡፡ ይህ ሕግ የጫካ ቡናዎችን ወደ አውሮፓ እና ሌሎች ዓለም ገበያ መዳረሻዎች የምትልከው ኢትዮጵያን እንደሚመለከት ስጋቶች ተነስተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ጉዳዩ እንዳሳሰበው ገልጾ አዲሱ የአውሮፓ ህግ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ እንዲረዳ ካልተደረገ ሚሊዮኖች ወደ ድህነት ሊወርዱ ይችላሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሁሴን አምቦ (ዶ/ር) ለአልዐይን እንዳሉት “በኢትዮጵያ ቡና…
Read More
የጀርመኑ ናቡ የተሰኘው የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የአፍሪካ ቢሮውን በኢትዮጵያ ከፈተ

የጀርመኑ ናቡ የተሰኘው የአካባቢ ጥበቃ ተቋም የአፍሪካ ቢሮውን በኢትዮጵያ ከፈተ

ከ125 ዓመት በፊት የተመሰረተው የጀርመኑ የተፈጥሮ እና ብዝሀ ህይወት ጥበቃ ተቋም (ናቡ) የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከፍቷል፡፡ የናቡ ፕሬዝዳንት ጆርግ አንድሪያስ ክሩገር እንዳሉት ኢትዮጵያ የብዝሃ ህይወት ሀብት በብዛት ከሚገኙባቸው ሀገራት መካከል አንዷ በመሆኗ እና ከአፍሪካ ጋር ለሚኖረን ግንኙነት መግቢያ በመሆኗ ቢሯቸውን በአዲስ አበባ ለመክፈት እንደወሰኑ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እና ተቋማት ጋር ያለንን ግንኙነት በማቀላጠፍ ተጨማሪ የተፈጥሮ እና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ስራዎችን ለማስራት ቢሯችንን በአዲስ አበባ ለመክፈት አነሳስቶናልም ብለዋል፡፡ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረው ይህ የተፈጥሮ እና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ተቋም በአውሮፓ፣ እስያ እና አፍሪካ ሀገራት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ7 ሀገራት ላይ እየሰራ…
Read More
በደላንታ ኦፓል በማውጣት ላይ እያሉ የተቀበሩ 20 ወጣቶችን ለማትረፍ ህዝቡ ሌት ተቀን እየቆፈረ ነው ተባለ

በደላንታ ኦፓል በማውጣት ላይ እያሉ የተቀበሩ 20 ወጣቶችን ለማትረፍ ህዝቡ ሌት ተቀን እየቆፈረ ነው ተባለ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ልዩ ስሙ አለኋት ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነበር ኦፓል ማዕድን በማውጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች መውጫ ስፍራ በአለት የተደፈነባቸው፡፡ በማህበር ተደራጅተው ኦፓል እንዲያወጡ የተደራጁት እነዚህ ወጣቶች ቁጥራቸው 20 ሲሆን ከመሩት በህይወት ለማትረፍ የአካባቢው ማህበረሰብ ሌት ተቀን በፈረቃ እየቆፈረ መሆኑን የዞኑ መንግስት ኮሙንኬሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ እያሱ ለአልዐይን ተናግረዋል፡፡ እንደ አቶ እያሱ ገለጻ ከሆነ ወጣቶቹ ሌሊት ላይ ማዕድኑን ለማውጣት እየቆፈሩ እያሉ መውጫቸው በዓለት የተዘጋ ሲሆን በአካባቢው የነበሩ በተመሳሳይ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ጉዳዩን ለህዝብ አሳውቀዋል፡፡ ጥር 30 ቀን የተከሰተው ይህ አደጋ ከመሬት ውስጥ ባለው ዋሻ ውስጥ ያሉትን ወጣቶች የደላንታ ወረዳ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በዘመቻ…
Read More
በኢትዮጵያ የሚገኘው ባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

በኢትዮጵያ የሚገኘው ባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እንዳስታወቀው የኢትዮጲያው ጥቁር ጎፈር አንበሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እየተመናመነ በመምጣቱ የመጥፋት አደጋ ተጋረጦበታል ተብሏል፡፡ በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ እንደተናገሩት ህገወጥ የነዋሪዎች ሰፈራ፣ የደን ጭፍጨፋ መኖር፣ የእርሻ ስራ እና  ግጦሽ  መበራከት የእንስሳቶቹ ስፍራ እንዲወድም ያደረጉ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው። በዚህም አንበሳን ጨምሮ የዱር እንስሳት የሚፈልጉትን ምግብ እንዳያገኙና በምግብ ሰንሰለት ውስጥ ችግር እንዲፈጠር ብሎም ለህገወጥ አደን  በስፋት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ሲሉ አክለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የተለየ የአንበሳ ዝርያ ነው ተብሎ የሚታወቀው እና የመጥፋት አደጋ ያጠላበት የጥቁር ጎፈር አንበሳ  ቆዳም በአብዛኛው  በኬንያ ፣በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን በኩል የህገወጥ ዝውውር …
Read More
ሱዳን የኢትዮጵያ 70 ሚሊዮን ዶላር የኤሌክትሪክ እዳ እንዳለባት ተገለጸ

ሱዳን የኢትዮጵያ 70 ሚሊዮን ዶላር የኤሌክትሪክ እዳ እንዳለባት ተገለጸ

ጎረቤት ሀገር ሱዳን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ከሚገዙ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ለዓመታት የተጠቀመችበትን እዳ አልከፈለችም ተብሏል፡፡ ሱዳን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተጠቀመችበትን 70 ሚሊዮን ዶላር እዳዋን ባለመክፈሏ ምክንያትም የሚቀርብላት የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን በ50 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡ ካሳለፍነው ሚያዚያ ወር ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ሱዳን ከ8 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ግብጽ  እና ቻድ ደግሞ ሱዳናዊያን የተጠለሉባቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ለጎረቤት ሀገራት ከሸጠችው የኤሌክትሪክ ሽያጭ 66 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 47 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የፌደራል ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል። ሱዳን ባለባት የጸጥታ ችግር ምክንያት ከዚህ በፊት የተጠቀመችበትን የኤሌክትሪክ ኃይል ክፍያ በወቅቱ መክፈል አለመቻሏ ለገቢው…
Read More
በኢትዮጵያ ግዙፉ የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተባለ

በኢትዮጵያ ግዙፉ የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በ5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ ከሁለት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል። የከሰል ማዕድን አምራቹ ኢቲ ማይኒንግ ፋብሪካ እንደሚሰኝ ሲገለፅ ፋብሪካው 150 ቶን ከሰል በሰዓት የማምረት አቅምና የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን 75 በመቶ የድንጋይ ከሰል ፍላጎት ለማሟላት ያስችላል ተብሏል። የፋብሪካው ፕሮጀክት ማናጀር ኢንጅነር በላይ አሰፋ የኢትዮጵያ የታጠበ ከሰል ፍላጎት ሀገሪቱ በዓመቱ በአማካይ 400 ሚሊዮን ዶላር እያሳጣት መሆኑን ገልፀዋል። ይህ ፋብሪካ ከሁለት ዓመት በፊት ተጀምሮ በአሁኑ ጊዜ አጠቃላይ ሥራው እየተጠናቀቀ በመሆኑ በፋብሪካው የሚሠሩ ቋሚ ሠራተኞች ሥልጠና እየተሰጠና የሙከራ ሥራዎች ከተሠሩ በኋላ ከሁለት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተመርቆ ሥራ ይጀምራል ተብሏል።…
Read More
ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ልትከለክል መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ልትከለክል መሆኗን ገለጸች

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር የስድስት ወራት ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ሚኒስትሩ አቶ አለሙ ስሜ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ የሚደረገው ክልከላ ሙሉ ለሙሉ ተፈፃሚ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ አቶ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ለፓርላማው እንደተናገሩት፥ ነዳጅ የሚወስዱ ተሽከርካሪዎችን ለግል ጥቅማጥቅ ሆነ ለሌላ አላማ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚደረገውን እገዳ በጥብቅ እንደሚያስፈጽሙ ገልጸዋል። ውሳኔው ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ስጋቶች እና ከባህላዊ የነዳጅ ፍጆታ ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለሚመጣው ወጭ ስልታዊ ምላሽ ነውም ተብሏል። እየጨመረ የመጣው የነዳጅ ወጪ ፖሊሲ አውጪዎች አገሪቱ በተለመዱት ተሽከርካሪዎች ላይ ያላትን ጥገኝነት እንዲገመግሙ እና የካርበን በካይ ጋዝ መጠንን ለመቀነስ ከሚደረገው…
Read More
ኢትዮጵያ በቮልስዋገን ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

ኢትዮጵያ በቮልስዋገን ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

በቮልስ ዋገን አይዲ ሲሪየስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱ ተገልጿል፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ቮልስ ዋገን አይዲ ሲሪየስ (ID Series) የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ እገዳ ጥላ ነበር፡፡ ከቻይና ተገጣጥሞ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የነበረው የጀርመን ምርት የሆነው ቮልስ ዋገን ተሽከርካሪ ባትሪው ከኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጋር የሚጣጣም አይደለም በሚል በቀረበው ቅሬታ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ታግዶ ቆይቷል፡፡ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሕዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪና ተሽከርካሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አበራ ሞሲሳ እንዳሉት፤ የጀርመን መንግሥት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ መሠረት ቮልስ ዋገን ተሽከርካሪ እንዳይገባ ተደርጎ ቆይቷል፡፡ ደብዳቤው የተሽከርካሪዎች ባትሪ ከኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጋር የማይጣጣም…
Read More
የምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው

የምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው

600 ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚደረግበት 300 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሊገነባ ነው፡፡ የንፋስ ሀይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ስምምነት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቱ አሜአ ፓወር ኩባንያ ጋር የስምምነት ፊርማ በዱባይ ተፈራርሟል፡፡ በሶማሌ ክልል አይሻ አካባቢ የሚገነባው የንፋስ ሀይል ማመንጫ 300 ሜጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው እንደሆነ ተገልጿል። አጠቃላይ የንፋስ ሀይል ማመንጫው 600 ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚደረግበት ሲሆን አሜአ ፓወር በተሰኘ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኩባንያ እንደሚገነባ ተጠቅሷል፡፡ ስምምነቱ በመንግስትና በግል አልሚዎች ማእቀፍ የሚሰራ ትልቁ ኢንቨስትመንት እንደሚሆን እንዲሁም በንፋስ ሀይል ማመንጫ ከምስራቅ አፍሪካ ግዝፉ ይሆናል ተብሏል። ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል ፍላጎቷን ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ሀይል…
Read More