አካባቢ ጥበቃ

የ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቀቀ

የ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቀቀ

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቀቀ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት  እንዳስታወቀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቋል። የሕዳሴ ግድብ መሠረተ ድንጋይ የተጣለበት 12ኛ ዓመትን አስመልክቶ ጽህፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ግድቡ በሚቀጥለው ዓመት ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን 5200 ሜጋ ዋት ሀይል ያመነጫል። በ5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እየተገነባ ያለው ይህ የአፍሪካ ግዙፍ ግድብ ወጪው በኢትዮጵያውያን እና በመንግስት በመሸፈን ላይ ይገኛል። የግድቡ ሁለት ቱርባይኖች አሁን ላይ 700 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት ላይ ሲሆን የግድቡ አራተኛ ዙር ውሀ ሙሌት በመጪው ክረምት ወራት እንደሚካሄድ ተገልጿል። ግብጽ ኢትዮጵያ በተናጥል በግድቡ ላይ የምትወስደው እርምጃ ታሪካዊ የውሀ ድርሻዬን ይጎዳል በሚል…
Read More
ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪዋን በሞት አጣች

ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪዋን በሞት አጣች

ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ተመራማሪዋን በሞት አጣች ታዋቂው የአካባቢ ጉዳይ ሳይንስቲስት ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገብረእግዚአብሄር በ 83 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፋል። ዶ/ር ተወልደብርሃን በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ አቅራቢያ ባለችው ‹‹አዲ-ስላም›› የተሰኘች የገጠር መንደር  የተወለዱ ሲሆን ፣ በቀለም ትምህርት ገፍተው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ1955 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተቀበሉ በኋላ የሁለተኛ እና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከዌልስ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡ በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ አገልግሎት የተከበረ ሥም ያላቸው ዶክተር ተወልደ በዘርፉ ላደረጉት ምርምርና በጉዳዩ ዙሪያ ከፍተኛ ግንዛቤ እንዲፈጠር ላደረጉት ጥረት በ2000 Right Livlihood Award ሽልማት አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በ2006 ዓመት የተባበሩት መንግሥታት በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጠውን Champions of the Earth ሽልማት አግኝተዋል፡፡ የተማሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ…
Read More
ኡጋንዳውያን የዓለም ፍጻሜ ደርሷል በሚል ወደ ኢትዮጵያ መፍለሳቸው ተገለጸ

ኡጋንዳውያን የዓለም ፍጻሜ ደርሷል በሚል ወደ ኢትዮጵያ መፍለሳቸው ተገለጸ

በመቶዎች የሚቆጠሩ የኡጋንዳ የሐይማኖት ኑፋቄ አባላት የምፅዓት ቀንን በመስጋት ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ ነው ተብሏል፡፡ የኑፋቄ መሪዎቹ የዓለም መጨረሻ እንደቀረበና ሞትም አካባቢያቸውን እንደሚመታ አሳምኗቸዋል። በኡጋንዳ ምስራቃዊ ክፍል ውስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቀያቸው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን የኡጋንዳ ፖሊስ አስታወቋል። ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የኑፋቄው አባላት ከአካባቢያቸው ይጀመራል ብለው ካመኑበት የዓለም ፍጻሜ ለማምለጥ ሸሽተዋል ብሏል። የኑፋቄው አባላት በቅርቡ አካባቢያቸው በሞት እንደሚመታ እና ሁሉም ሰዎች እንደሚሞቱ በመሪዎቹ እንደተነገራቸው ገልፀዋል። ንብረታቸውን ሸጠው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸው የተነገረው አነዚህ ኡጋንዳውያን ከዚያም ካሉበት በኡጋንዳ ከሚገኙ አንዳንድ ዘመዶቻቸው ጋር እየተነጋገሩ ነው። “የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ቤተክርስቲያን በሚባል የሃይማኖት ኑፋቄ ላይ በኡጋንዳ ምስራቃዊ ሴሬሬ ወረዳ በኦቡሉም መንደር ውስጥ የሚገኘውን የሃይማኖት ክፍል…
Read More