23
Mar
የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቀቀ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 90 በመቶ ተጠናቋል። የሕዳሴ ግድብ መሠረተ ድንጋይ የተጣለበት 12ኛ ዓመትን አስመልክቶ ጽህፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ግድቡ በሚቀጥለው ዓመት ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን 5200 ሜጋ ዋት ሀይል ያመነጫል። በ5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እየተገነባ ያለው ይህ የአፍሪካ ግዙፍ ግድብ ወጪው በኢትዮጵያውያን እና በመንግስት በመሸፈን ላይ ይገኛል። የግድቡ ሁለት ቱርባይኖች አሁን ላይ 700 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት ላይ ሲሆን የግድቡ አራተኛ ዙር ውሀ ሙሌት በመጪው ክረምት ወራት እንደሚካሄድ ተገልጿል። ግብጽ ኢትዮጵያ በተናጥል በግድቡ ላይ የምትወስደው እርምጃ ታሪካዊ የውሀ ድርሻዬን ይጎዳል በሚል…