27
Jun
በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ሀብት ላይ ከተደቀኑ በርካታ ችግሮች መካከል ህገወጥ የእንስሳት ዝውውር አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ እንደተናገሩት ለተለያዩ አላማዎች ሲባል በኢትዮጵያ የሚገኙ የዱር እንስሳት ከነህይወታቸው በህገወጥ መንገድ ይዘዋወራሉ። በዚህ መልኩ ከሀገር የሚወጡ እንስሳቶች በርካታ ቢሆኑም በቀዳሚነት አቦሸማኔ ይጠቀሳል ። አቦሸማኔ በተለይም በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሱማሌ ክልል መኖሪያውን በማድረጉ የአካባቢው ማህበረሰቦች ባካበቱት ተፈጥሮአዊ ዘዴ የአቦ ሸማኔ ቡችላዎችን በመያዝ ሶማሌላንድ አካባቢ ለሽያጭ እንደሚያቀርቡ ተጠቁሟል። በዚህ መልኩ ይህ እንስሳ ወደ መካከለኛው የአረብ ሀገራት ጭምር ላሉ ባለሀብቶች የሚሸጥበት ሁኔታ መኖሩን የገለፁት አቶ ዳንኤል ግለሰቦቹ የራሳቸው የሆነ መካነ አራዊት…