ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመረቀች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኬንያው ፕሬዚዳንት ውሊያም ሩቶ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኢል ኦማር ጊሌ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር በተገኙበት የዓባይ ግድብ መርቀዋል።

የኢትዮጵያ የዓባይ ግድብ የምረቃ ሥነስርዓት ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓም ሲካሄድ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

የዓባይ ግድብ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ 233 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደገ ሲሆን፤ ቦንድ በመግዛት፤ ስጦታ በመስጠት እና በሌሎች መንገዶች ህዝብ ትልቅ ተሳትፎ እንዳደረገ በስፋት ተግልጿል፡፡

ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት የህዳሴ ግድቡ መጠናቀቅም የኢትዮጵያን አቅም በሁሉም ዘርፍ የሚያሳግ እንደሆነም የተለያዩ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ዓባይ ግድብ የሚገኘው በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ ሲሆን ግድቡ ግንባታ የተጀመረው መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ነው፡፡

ግድቡ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ሲኖረው የግድቡ የውሃ የመያዝ አቅም 74 ትሪሊዮን ሊትር ውሃ ነው።

የግድቡ ከፍታ ርዝመት 145 ሜትር ሲሆን የግድቡ የጎን ርዝመት 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር መሆኑን ታውቋል።

በግድቡ ምክንያት የተፈጠረው ሀይቅ ንጋት የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ከ80 በላይ ደሴቶችን ፈጥሯል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይም የተለያዩ  ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በግድቡ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡማር ጌሌ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ፣የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት፣ የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሴል ሚሶ ድላሚኒ፣ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አሞር ሞትሊ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ  እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 150 ዓመታትን እንዲያገለግል ታስቦ የተገነባ ሲሆን በደለል እንዳይሞላ የተፈጥሮ ጥበቃ ስራዎች ከተሰራለት አገልግሎቱን እስከ 350 ዓመታት ድረስ ማራዘም እንደሚቻል ምሁራን ይናገራሉ።

እንዲሁም 40 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ እርሻ መሬት በአባይ ተፋሰስ ስር የሚገኝ ነው።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *