መነሻ ገፅ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ

ከአንድ ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር የወደብ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ስምምነቱን ተከትሎ ሶማሊያ ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው በሚል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣም ነበር፡፡ የሁለቱም ሀገራት ወዳጅ የሆነችው ቱርክ በአንካራ የውይይት መድረክ ያዘጋጀች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በትናንትናው ዕለት ወደ አንካራ አቅንተው ነበር፡፡ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የሁለቱን ሀገራት መሪዎች በተናጠል አግኝተው እንዳወያዩ አናዶሉ ዘግቧል፡፡ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ኢትዮጵያ እና ሱማልያ ሀለቱንም ሀገራት በሚያግባባ መልኩ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል። ኤርዶጋን ሁለቱ ሀገራት በጋራ ይፋ የሚያደርጉት የስምምነት ዶክመንት እንደተዘጋጀ ጠቅሰው ዶክመንቱ ሀገራቱ የበፊቱን ሳይሆን መጪውን ግዜ እንዴት በጋራ አብረው ተከባብረው እና በመልካም ጉርብትና እንደሚወጡት…
Read More
ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀም ጀመረች

ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀም ጀመረች

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስቴር ዛሬ በሶማሌላንድ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎች ስራ መጀመራቸውን ገልጿል። የሶማሌላንድ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዲረሺድ ኢብራሂም ደግሞ  "የሶማሌላንድ መንግሥት በበርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎችን ስራ አስጀምሯል " ሲል ይፋ አድርገዋል። "ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ውጥን ቀጠናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ሶማሌላንድ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ አክለዋል። ቢሮው በወደቡ የሚራገፉ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ መዳረሻዎች እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነውም ተብሏል። በርበራ ወደብ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትሱ DP World ይተዳደራል የተባለ ሲሆን የበርበራ ወብ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስፓቺ ዋታንቫራቺ ተገኝተው…
Read More
በኢትዮጵያ የአንበሳ እንስሳት የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበታል ተባለ

በኢትዮጵያ የአንበሳ እንስሳት የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበታል ተባለ

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን  የአንበሳ እና የስጋ በል እንስሳት ተመራማሪ የሆኑት አቶ ካህሳይ ገብረ-ተንሳይ  አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያሉት አንበሶች ቁጥር ከ1 ሺ እንደማይበልጥ ተናግረዋል። በሃገሪቱ አሁን ላይ አንበሶች ያሉበት  ሁኔታ ለማወቅ ጥናት  ማድረጋቸውን የገለፁልን ተመራማሪው በአዋሽ  እና በመካከለኛው አዋሽ  በተደረገው ጥናት መሰረት ያለው ሁኔታ  ተስፋ ሰጪ ቢሆንም   አሁንም ግን ሁሉም ርብርብ ካላደረገ  አንበሶቹን ልናጣ እንችላለን ብለዋል፡፡ ተመራማሪው እንደሚሉትም ህገወጥ የነዋሪዎች ሰፈራ፣ የደን ጭፍጨፋ መኖር፣ የእርሻ ስራ እና  ግጦሽ  መበራከት አንበሶቹ  የሚፈልጉትን ምግብ እንዳያገኙና በምግብ ሰንሰለት ውስጥ ችግር እንዲፈጠር ብሎም ለህገወጥ አደን  በስፋት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ  የባህል መድኃኒት ቀማሚዎች  ፊታቸውን ወደ አንበሳ አጥንት ማዞራቸው እንስሳቶቹን ለህገወጥ…
Read More
ዳሸን ባንክ ዘ ባንከር የተሰኘውን ሽልማት አሸነፈ

ዳሸን ባንክ ዘ ባንከር የተሰኘውን ሽልማት አሸነፈ

ዳሸን ባንክ በተለያዩ ዘርፎች ባስመዘገበው የላቀ አፈጻፀም የ“ዘባንከር” ሽልማት ተሸላሚ ሆነ ባንኮችን በተለያዮ የምርጥ አፈጻጸም መለኪያዎች የሚመዝነው የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ የሚያሳትመው ዘባንከር መጽሔት ዳሸን ባንክ የ2024 የኢትዮጵያ አሸናፊ ሆኗል፡፡  የዳሸን ባንክ ቺፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን ወ/ሪት እየሩሳሌም ዋጋው እና የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የፋይናንስ ዘርፍ አማካሪ አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በእንግሊዝ ሎንዶን ተገኝተው ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡  በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለፀው ዳሸን ባንክ በዘርፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማቅረብ እና ከተለያዩ አለምአቀፍና አህጉራዊ ባለድርሻ አካላት ጋር የፈጠረው ውጤታማ ጥምረት ለሽልማት አብቅቶታል ተብሏል፡፡  አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ሽልማቱ ዳሸን ባንክ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካኝነትና እና ከተለያዩ አለም አቀፍና አህጉራዊ ተቋማት…
Read More
ለአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ምርጫ ሶስት ዕጩዎች ይፋ ሆኑ

ለአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ምርጫ ሶስት ዕጩዎች ይፋ ሆኑ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ምርጫ በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት የህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃማት ስልጣን ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት ቀርቶታል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ባሳለፍነው ነሀሴ ባወጣው ማስታወቂያ የህብረቱ አባል ሀገራት እጩዎች እንዲመዘገቡ በጠየቀው መሰረት ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ማዳጋስካር እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ዕጩ አቅርበው ጸድቆላቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የኬንያ ፕሬዝዳንት ለመሆን አራት ጊዜ ተወዳድረው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በይፋ የህብረቱ ሊቀመንበር ምርጫ ተወዳዳሪ ከሆኑት መካከል አንዱ ሆነዋል፡፡ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የራይላ ኦዲንጋ ጥያቄን በአዲስ አበባ በይፋ ያስተዋወቀ ሲሆን የምረጡኝ ቅስቀሳውን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከኬንያ በተጨማሪም የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀሙድ አሊ የሱፍ እና የቀድሞ የማዳጋስካር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ…
Read More
መንግስት ታዳጊዎችን በግዳጅ ለውትድርና እየመለመለ ነው ተባለ

መንግስት ታዳጊዎችን በግዳጅ ለውትድርና እየመለመለ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት የመከላከያ ሰራዊት አባል ለመሆን የሚፈልጉ ዜጎችን ምልመላ አስመልክቶ ያደረገውን ምርመራ ይፋ አድርጓል፡፡ ከሚሽኑ ምርመራውን በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፣ በቢሾፍቱ፣ በጅማ እና በሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ እጩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማቆያ ስፍራዎችን በመጎብኘት፤ በማቆያ ስፍራዎቹ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን በጉዳዩ ዙሪያ ቃለ መጠይቅ ማድረጉን ገልጿል። የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርም የመከላከያ ሰራዊት ምልመላ ሂደቱን በመከላከያ ሚኒስቴር መስፈርቶች መሠረት እንዲያከናውን መጠየቁን እንደተረዳ ኮሚሽኑ አስታውቋል። ይሁንና የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር አካላት እና የጸጥታ ኃይሎች አባላት በመከላከያ ሚኒስቴር ከተገለጸው የምልመላ መስፈርት ውጪ ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን “የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ” በሚል በግዳጅ እንደያዙ…
Read More
ኢትዮጵያ 10 የኢንዱስትሪ ፓርኮቿን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንነት አሳደገች

ኢትዮጵያ 10 የኢንዱስትሪ ፓርኮቿን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንነት አሳደገች

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስፈላጊዉን መስፈርት አሟልተዋል ያላቸዉን 10 ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን እንዲያድጉ መወሰኑ ተገልጿል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበኩሉ እንዳስታወቀው በስሩ ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መካከል 10ሩ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማደጋቸውን አሳዉቋል። አሁን በስራ ላይ ካሉ 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያደጉት አዳማ ባህርዳር ፣ ቦሌ ለሚ ፣ ደብረ ብረሃን እና ሀዋሳ ፣ ጅማ ፣ ቂሊንጦ ፣ ኮምቦልቻ ፣ መቀሌ እና ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ መሆናቸው ታዉቋል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለማሳደግ አዋጅ ቁጥር 1322/2016 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል። ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ…
Read More
ዝነኛው የኢትዮጵያ ሙዚቀኛ ማሕሙድ አሕመድ ከመድረክ ሊሰናበት ነው

ዝነኛው የኢትዮጵያ ሙዚቀኛ ማሕሙድ አሕመድ ከመድረክ ሊሰናበት ነው

በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያደረገው ጋሽ ማህሙድ አህመድ ማይኩን ሊሰቅል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ማህሙድ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ዕድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የክቡር ዶክተር ማዕረግን መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፍ ዝነኛ  የሆነውን የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም የመሰናበቻ ፕሮግራም በአዲ አበባ እና በአሜሪካ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል፡፡ የመሰናበቻ ሙዚቃ ፕሮግራም ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲ አበባ ሚለኒየም አዳራሽ የድምጻዊ ማሕሙድ አሕመድ የመጨረሻ የህይወት ዘመን ስንብት ደማቅ ኮንሰርት እንደሚዘጋጅ ተነግሯል ፡፡ በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይም የክቡር ዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት ላይ የተዘጋጀ መፅሀፍ እንደሚመረቅም ተገልጿል፡፡…
Read More
ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር የነበሩት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ስለሺ በቀለ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ መልቀቂያ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ አምባሳደር ስለሺ በቀለ  በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደርነት ሹመታቸው መልቀቂያ ካስገቡ በኋላ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ሌንጮ ባቲ ይተኳቸዋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ይሁንና አሜሪካ የአምባሳደር ሌኝጮን ሹመት መቃወሟን ተከትሎ ብናልፍ አንዷለም በዋሸንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡ የቀድሞው የአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ መምህር ስለሺ በቀለ በአምባሳደርነት ከመሾማቸው በፊት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው ከአምስት ዓመት በላይ አገልግለዋል፡፡ አምባሳደር ሽለሺ በታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ቃለ መጠይቅ በመስጠት የሚታወቁ ሲሆን በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና…
Read More
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ

28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የባንኩ ሪፖርት እስከ ሰኔ 2024 ድረስ ያሉ የገንዘብ እንቅስቀሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው 28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን አጥተዋል ብሏል፡፡ የማጭበርበር ድርጊቶቹ የተፈጸሙት በሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ በተሰረቁ የኤትኤም ማሽኖች፣ በሐሰተኛ ቼኮች፣ በሐሰተኛ የስልክ መልዕክት እና ተያያዥ መንገዶች አማካኝነት ነው፡፡ በዚህ ዓመት ባንኮች ያጡት ገንዘብ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ እንዳሳየም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ካሉ 31 ባንኮች ውስጥ 28ቱ ሲጭበረበሩ የቀሪዎቹ ሶስት ባንኮች ማንነት ግን በሪፖርቱ ላይ አልተጠቀሰም፡፡ ባንኮች ከአነስተኛ የብድር እና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ብድሮችን እየሰጡ…
Read More