Blog

ኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘቧን በ31 በመቶ አዳከመች

ኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘቧን በ31 በመቶ አዳከመች

ኢትዮጵያ ከዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ ማድረግ ጀምራለች፡፡ ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በዲሱን የምንዛሬ ተመን ዛሬ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ማሻሻውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫው የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወስንበት የገበያ ሥርዓት መሸጋገሩን አስታውቋል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ74.7364 ብር እየተገዛ በ76.2311 እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል። ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ የ18 ብር ጭማሪ ታይቷል። በኢትዮጵያ ንግድ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ቢሊዮን ዶላር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ቢሊዮን ዶላር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ 7 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሰጠው መግለጫ በተያዘው በጀት ዓመት 7.02 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል። የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ ይህ ትርፍ ከባለፈው ከመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል። ትርፉ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 402 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። ስራ አስፈጻሚው እንደገለጹት አየርመንገዱ 577,746 የበረራ ሰአቶችን ማስመዝገቡን እና ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ጭማሪ አለው።  በበጀት አመቱ 17.1 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዱን የገለጸው አየር መንገዱ ከእነዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑት አለምአቀፍ መንገደኞች ሲሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑን ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ናቸው ብሏል።…
Read More
በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን በደረሰው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ ባወጣው የሁኔታዎች መግለጫ ላይ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል አመልክቷል። እሁድ ሐምሌ 14 እና ሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ተቀብረው የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ዛሬም ለአራተኛ ቀን እየተካሄደ ነው። በአደጋው ስፍራ ዛሬን ጨምሮ በአካባቢው እየጣለ ባለው ዝናብ ውስጥ ጭምር ከተንሸራተተው መሬት ስር ለማውጣት የሚደረገው የነፍስ አድን ጥረት ቀጥሏል።…
Read More
በኢትዮጵያ በመሬት መንሸራተት አደጋ ከ260 በላይ ዜጎች ሞቱ

በኢትዮጵያ በመሬት መንሸራተት አደጋ ከ260 በላይ ዜጎች ሞቱ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከትናንት በስቲያ በደረሰ የመሬት ናዳ አደጋ የሞቱ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን እስከ ትንናት ምሽት ድረስ የሟቾች ቁጥር 229 ነበር። የገዜ ጎፋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ የሟቾች ቁጥር ወደ 260 ማሻቀቡን ተናግረዋል። እስካሁን በተደረገው ፍለጋ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ በድምሩ የ260 ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን፣ የአስክሬን ፍለጋ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን  ተናግረዋል። አደጋው መጀመሪያ ሶስት ቤተሰብ ላይ…
Read More
ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀገሯ እንዳይበር አገደች

ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀገሯ እንዳይበር አገደች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ከመስከረም ወር ጀምሮ አየር መንገዳችን ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱን አሳውቆናል” ብሏል፡፡ ኤርትራ የትራንስፖርት እና ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስቴር የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀጣዩ መስከረም በኋላ ወደ አሥመራ እንዳይበር ማገዱን የሚያሳውቅ ማስታወቂያ በዛሬው እለት አውጥቷል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን አስመለክቱ በሰጠው መግለጫ፤ “የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ሐምሌ 14 2016 ዓ.ም ወይም በፈረንጆቹ 21 ጁላይ 2024 በላከው ደብዳቤ በፈረንጆቹ ከመስከረም 30 ቀን 2024 ዓ.ም. ጀምሮ አየር መንገዳችን ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱን አሳውቆናል” ብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳዩን አስመልክቶ የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ጉዳዩም በበጎ መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ያለውን…
Read More
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ተመረጠ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ተመረጠ

የአሜሪካው አለምአቀፍ የስፓርት ቻናል (ኢኤስፒኤን) ቀነኒሳ በቀለን የ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ አትሌት ነው ሲል መርጦታል፡፡ የስፖርት ቻናሉ ከቀነኒሳ በቀለ በተጨማሪ ሌላኛዋ ኢትዮጵያት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ በ21ኛው ክፍለዘመን ምርጥ ያላቸውን የአፍሪካ ስፓርተኞች ይፋ አድርጓል። ኢኤስፒኤን አህጉሪቱ ካላት ስፋት እና የስፖርት ብዛት አንጻር 25 ምርጥ አትሌቶችን መምረጥ ከባድ መሆኑን አስታውቋል። ዓለም ካየቻቸው ምርጥ የማራቶን ሯጭ አንዱ ከሆነው ኢሉድ ኪፕቾጌ እና ኦሎምፒክ እና በርካታ የአውሮፓ ሻሜፒዮን ሽፕ አሸናፊ ከሆነው ሳሙኤል ኢቶ ማንን ትመርጣላችሁ? ሲልም ኢኤስፒኤን ይጠይቃል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቻናሉ ዘገባ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ የአፍሪካ ስፖርተኛ ተብሎ ስሙ በመካተቱ እንደተደሰተ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ ጽፏል። አትሌት ቀነኒሳ በ2000ዎቹ በ10ሺ እና በ5ሺ ሜትር…
Read More
አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ

አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ

ቦብ ሜንድዝ ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ የሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ የዘር ሀረጋቸው ከኩባ የሚመዘዘው ሜንድዝ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት የኒው ጀርሲዋን ዩኒየን ሲቲን በከንቲባነት አገልግለዋል፡፡ እኝህ ጉምቱ ፖለቲከኛ በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አድርገዋል ተብሏል፡፡ እንደ አሜሪካ ድምጽ ዘገባ ከሆነ ፖለቲከኛው ይህን ያደረጉት ከግብጽ ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጉቦ ከተቀበሉ በኋላ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ…
Read More
የፓሪስ ክለብ እና ቻይና ኢትዮጵያ አዲስ ብድር እንድታገኝ ፈቀዱ

የፓሪስ ክለብ እና ቻይና ኢትዮጵያ አዲስ ብድር እንድታገኝ ፈቀዱ

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ ሊሰጠው ያሰበውን ብድር እና እርዳታ የከለከለው፡፡ ጦርነቱ እንዲቆም ያደረገው የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የቆመውን ጨምሮ አዲስ ብድር እንዲሰጣት ለተቋሙ ጥያቄ ያቀረበች ቢሆንም በተደጋጋሚ የተደረጉ ውይይቶች የታሰበውን ያህል ፍሬ ሳያፈሩ ቆይተዋል፡፡ አይኤምኤፍ በድር ለኢትዮጵያ ከመፍቀዱ በፊት 20 አባላት ያሉት ፓሪስ ክለብ በመባል የሚጠራው የበለጸጉ ሀገራት ስብስብ ብድር እንዲሰጥ ይሁንታ እንዲሰጥ ሲጠበቅ ነበር፡፡ የሀገራትን ብድር የመክፈል አቅም በመገምገም ውሳኔ የሚሰጠው ይህ ስብስብ የኢትዮጵያንም አቅም ሲገመግም ቆይቶ ለአይኤምኤፍ ፈቃድ እንደሰጠ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ከፓሪስ ክለብ በተጨማሪም ሌላኛዋ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ብድር የሰጠችው ቻይና ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ተጨማሪ ብድር እንዲሰጣት ይሁንታቸውንን ሰጥተዋልም…
Read More
የኢትዮጵያ ውጪ ንግድ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

የኢትዮጵያ ውጪ ንግድ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ ነበር፡፡ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቋል፡፡ የተገኘው ገቢ ባለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው 3 ነጥብ 64 ቢሊየን ዶላር የ4.6 በመቶ ወይም በ166 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው፡፡ ከተገኘው ገቢ የግብርናው ዘርፍ 76 በመቶ በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ሲሆን ማኑፋክቸሪንግ ማእድን ፣ኤሌክትሪክና ሌሎች በተከታታይ የሚገኙ ናቸው። ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከ3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ከውጭ ሀገራት ግዢ በመፈጸም ለተጠቃሚዎች እንደተሰራጨም ተገልጿል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን…
Read More
ኢትዮጵያ የመንግስት ተቋማት አመራሮች ተጨማሪ ገቢ እንዳያገኙ የሚከለክል ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ የመንግስት ተቋማት አመራሮች ተጨማሪ ገቢ እንዳያገኙ የሚከለክል ህግ አዘጋጀች

የመንግስት አመራሮች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ ስራን መስራት እንዳይችሉ የሚደነግግ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ፡፡ የፌደራል የስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዳስታወቀው ማንኛውም የመንግስት አመራር ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ ንግድ እና መስል ስራዎችን መስራት የሚከለክል ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱን አስታውቋል። የመንግስት አመራሮች ለሙስና ተጋላጭ ናቸው ተብለው ከተለዩ ዘርፎች ውስጥ መሆናቸው የሚናገሩት የኮሚሽኑ የሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን በላይነህ በህዝብ ሃብት ላይ ውሳኔን የሚያሳልፉ አካላት የመንግስትና የህዝብን ስራ ብቻ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽኑ ለከፍተኛ ባለስልጣናት የጥቅም ግጭት መከላከል እና የሥነ-ምግባር ደንብ ረቂቅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን የሚናገሩት ሥራ አስፈፃሚው፤ አመራሮች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን ሲሰሩ የጥቅም ግጭቶች እንደሚከሰቱ እና አግባብ ባልሆነ መንገድ…
Read More