06
Sep
በአማራ ክልል ከትናንት በስቲያ ሰኞ ነሐሴ 29 ቀን 2015 የመንግሥት የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ እንዲሁም በድሮን ጥቃት ከ49 በላይ ንጹሃን መገደላቸውን እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ፓርቲው በመግለጫው ሰኞ ነሐሴ 29 ቀን 2015 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ ከተማ የመንግሥት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 29 ንጹሃን ዜጎች በየመኖሪያ ቤታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ብሏል፡፡ "ከሟቾች ውስጥም ሕጻናት፣ ወጣቶች እና አረጋውያን እንዳሉበት ከመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠናል።" ያለው ፓርቲው "በተመሳሳይ ነሐሴ 29 ቀን 2015 በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ፣ ሞሰባ ሽሜ አቦ ቀበሌ አዳራሽ ጎጥ ላይ መንግሥት በፈጸመው የድሮን ጥቃት ከ11 በላይ ንጹሐን ዜጎች ተጨፍጭፈዋል።" ብሏል። በዚሁ ቀን በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ…