01
Mar
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6 ኛውን ዙር ቀሪና ድጋሚ ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድባቸው አራት ክልሎች ምርጫ እንደሚያካሂድ ገልጿል፡፡ ምርጫ የሚካሄደው በጸጥታ እና በሌሎች ምክንያቶች ምርጫ ያልተካሄደባቸው አካባቢዎች ነው የተባለ ሲሆን የቤንሻንጉል ጉምዝ፤ አፋር፤ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 29 የምርጫ ክልሎች ውስጥ እንደሆነም ቦርዱ አስታውቋል፡፡ በዚህ ምርጫ ፕሮግራም ለዘጠኝ የተወካዮች ምክር ቤትና ለሃያ ስድስት የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ለማካሄድ እንደታቀደም ተገልጿል፡፡ ቦርዱ ባወጣው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ መሰረትም የእጩዎች ምዝገባ ከሚያዝያ 7 እስከ ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ/ም ይካሄዳል የተባለ ሲሆን የምረጡኝ ቅስቀሳ ደግሞ ከሚያዚያ 7 እስከ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ይካሄዳል፡፡ እንዲሁም የመራጮች ምዝገባ ደግሞ ከሚያዝያ 7 እስከ…