24
Sep
የመንግሥት አጠቃላይ የአገር ውስጥ የብድር ክምችት 2.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱን፣ ከዚህም ውስጥ የግምጃ ቤት ቦንድ ግዥ ከፍተኛ ድርሻ ይይዛል ተብሏል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር በዕዳ አስተዳደር ክፍል በኩል ያዘጋጀውን ወርኃዊ የዕዳ ማስታወቂያ የነሐሴ ወር 2017 ዓ.ም. ሪፖርት፣ የመንግሥት አገራዊ ብድር ዝርዝር መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መንግሥት እ.ኤ.አ. ከጁን 30 ቀን 2025 ጀምሮ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ብድር 2.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱን እንዳስታወቀ የሪፖርተር ዘገባ ያሳያል፡፡ ከአገር ውስጥ ብድር ድርሻ 80 በመቶ የሚይዘው በረዥም ጊዜ የሚከፈል የግምጃ ቤት ሰነድ እ.ኤ.አ. በኦገስት 2025 የግምጃ ቤት ሰነድ ግዥ ከፍተኛ እንደነበርና ከአጠቃላይ ክምችት አንፃርም 39 በመቶ እንደሚሸፍን ገልጿል፡፡ እስከ ኦገስት 2025 ድረስ ባለው የመንግሥት አጠቃላይ የአገር ውስጥ…