EthioNegari

አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በፕሬዝዳንት ትራምፕ አቀባበል ተደረገላቸው

አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በፕሬዝዳንት ትራምፕ አቀባበል ተደረገላቸው

አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተ-መንግሥት ተገናኝተው ተወያይተዋል ። በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተ-መንግሥት ተገናኝተው ተወያይተዋል። አምባሳደር ብናልፍ ነጩ ቤተ-መንግሥት ሲደርሱ በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲፕሎማሲያዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ይህ የመጀመሪያ ግንኙነት በቀጣይ ጊዜያት ለሚደረጉ ውይይቶች መጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል የተባለም ሲሆን፤ አምባሳደሩ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኝተው ስላደረጉት ውይይት በይፋ የተገለጸ ነገር የለም ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ በሁለቱ አገራት መካከል እንደ ሰላም፣ ጸጥታና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ከመፍጠር አንጻር ያሉ ዕድሎችም ሰፊ…
Read More
ሩሲያ ለኢትዮጵያ ባህር ሀይል ድጋፍ እያደረገች መሆኑ ተገለጸ

ሩሲያ ለኢትዮጵያ ባህር ሀይል ድጋፍ እያደረገች መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በሩሲያ ድጋፍ እያከናወነችው የሚገኘው የባህር ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ በሩሲያ ድጋፍ በአዲስ አበባ ከተማ ጃንሜዳ አካባቢ እያከናወነችው የሚገኘው የባህር ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታ 95 በመቶ መጠናቀቁ ተነግሯል። በሦስት ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የባህር ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ባለ አራት ፎቅ ሕንጻ ሲሆን፤ የአስተዳደር ቢሮዎች፣ የሕክምና ክሊኒክ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ያካተተ ስለመሆኑ ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል። ይህም ፕሮጀክት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ቀጣናዊ ተጽዕኖ መልሳ ለማግኘት የምትከተለው ሰፊ ስትራቴጂ አካል ነው የተባለ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ በታቀደለት ጊዜ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅም ተነግሯል። በተያዘው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ኢትዮጵያ የባህር…
Read More
ኢትዮጵያ ለእዳ ክፍያ 463 ቢሊዮን ብር መመደቧ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ለእዳ ክፍያ 463 ቢሊዮን ብር መመደቧ ተገለጸ

የገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሽዴ፣ ለ2018 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 93 ትሪሊዮን ብር ወይም 14 ቢሊዮን ዶላር ረቂቅ የፌደራል በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል። ረቂቅ በጀቱ እየተጠናቀቀ ካለው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ31 በመቶ ብልጫ ያለው ነው። ከቀረበው ረቂቅ በጀቱ ውስጥ 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮኑ ለመደበኛ ወጪ፣ 415 ቢሊዮኑ ለካፒታል ወጪ፣ 315 ቢሊዮኑ ለክልሎች ድጎማና 14 ቢሊዮኑ ለክልሎች የዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ እንዲውል መመደቡን ሚንስትሩ አብራርተዋል። ከጥቅል አገራዊ ምርት አንጻር 2 ነጥብ 2 በመቶ ያልተጣራ የበጀት ጉድለት ያጋጥማል ተብሎ እንደሚጠበቅና ኾኖም መንግሥት ጉድለቱን ለመሙላት ከብሄራዊ ባንክ ብድር እንደማይበደር ተገልጧል። ይህ በዚህ እንዳለ መንግስት ከያዘው በጀት አንድ ሶስተኛውን ለእዳ ክፍያ መያዙ…
Read More
አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ መፅሀፍ ተፃፈለት

አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ መፅሀፍ ተፃፈለት

የአትሌት ኃይሌን የህይወትና የስራ ፍልስፍና የሚያስረዳውን መፅሀፍ የፃፈችው ልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረስላሴ ናት። ረዳት ፀሀፊው ደግሞ አባዮሚ ሮቲሚ  የተባለ ፀሀፊ መሆኑን ሰምተናል። በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መጽሀፍ ለማሳናዳት ሁለት ዓመት እንደፈጀ ፀሀፊዋ አስረድታለች። አትሌት ኃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚያውቀው ቢሆንም መፃህፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነ ተነግሯል። ለዚህም ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ሀይሌ ህይወት ለማወቅና ለመፃፍ እንዳስቻላት ሜላት ኃይሌ ጠቅሳለች። መፅሀፉ አትሌት ከእድገቱ እስከ አሁን ባለው የሯጭነትና የቢዝነስ ምዕራፍ የተከተላቸውን አመለካከቶቹን፣ ፍልስፍናውን፣ የህይወት ልምዱ የተካተተበት መሆኑን ልጁ ሜላት ተናግራለች። ለጊዜው ''Dissecting Haile' በሚል ርዕስ ለህትመት የሚበቃው መፅሀፋ ወደፊት ወደ ወደ አማርኛ እና ሌሎች ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተነግሯል።…
Read More
በጋምቤላ ክልል ባለሀብቶች ህጻናትን በከብት እየለወጡ ነው ተባለ

በጋምቤላ ክልል ባለሀብቶች ህጻናትን በከብት እየለወጡ ነው ተባለ

በጋምቤላ ክልል በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ብሄረሰብ ታፍነው ለባርነት የሚወሰዱ ህፃናት መኖራቸውን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል። በቢሮው  የሕገ ወጥ ዝውውር ጽህፈት ቤት  አሰተባባሪ አቶ ኡቶው ቹሩ  እንደተናገሩት በዚህ መልኩ የሚወሰዱ ህፃናትን የማስመለስ ስራ ሲሰራ ቢቆይም ህገወጥ የህፃናት ዝውውርን ማስቀረት አልተቻለም ብለዋል። በደቡብ ሱዳን በኩል ያለው ድንበር  ክፍት መሆን በክልሉ ያሉ እና እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን በህገወጥ መልኩ ለመውሰድ አመቺ እንዳደረገው ገልፀው ባለሀብቶች ህፃናቱን በከብት የሚለውጡበት ሁኔታ መኖሩም ድርጊቱን እንዳይቆም ማድረጉን ተናግረዋል። አኙዋክ ብሔረሰብ ዞንን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ጎሳ ህፃናቱ እንደሚወሰዱ ተናግረዋል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከተወሰዱት ውስጥ በቅርቡ ሶስት ህፃናትን ማስመለስ መቻሉን የገለፁት አቶ ኡቶው በህይወት መኖራቸው ያልተረጋገጡ…
Read More
በኢትዮጵያ በቡና ላኪነት ለመሰማራት 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል ማስያዝ ግዴታ ሆነ

በኢትዮጵያ በቡና ላኪነት ለመሰማራት 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል ማስያዝ ግዴታ ሆነ

ከዚህ ቀደም የቡና ላኪነትን የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ይጠየቅ የነረበው የ1.5 ሚሊዮን ብር በ10 እጥፍ እንዲያድግ የተደረገው ዘርፉ በእውቀትና የተሻለ አቅም ባላቸው ሰዎች እንዲያዝ በማስፈለጉ ነው ተብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም በቡና ላኪነት የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ይጠየቅ የነበረው ካፒታል 1.5 ሚሊየን ብር ነበር፤ ይህ ገንዘብ አሁን በአስር እጥፍ እንዲያግ በኢትዮጵያ ቡና ሻይ ባለስልጣን ማሻሻያ መቅረቡ ተሰምቷል። የሚጠየቀው ካፒታል አነስተኛ ሆኖ በመቆየቱ አትራፊ ነው በሚል ብቻ ብዙዎች የሚገቡበት ዘርፍ ሆኖ ቆይቷል የሚሉት የኢትዮጵያ ቡና ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛት ወርቁ ናቸው። ይሄ ደግሞ እዚሁ ሀገር ቤት በአቅራቢ እና ላኪዎች እንዲሁም ላኪዎች እና የውጭ ገዥዎች መካከል ችግሮች እንዲፈጠሩ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።  የቡና_ንግድ ሰዎች የተወሰነ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ14 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ማጓጓዙን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ14 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ማጓጓዙን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት 9 ወራት 14.5 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙን አስታውቋል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ13 በመቶ እድገት እንዳለው ዋና ስራ አስፈፃሚው መስፍን ጣሰው ተናግረዋል፡፡ አየር መንገዱ በዘጠኝ ወር ውስጥ ያገኘው ገቢ 5.6 ቢሊዮን ዶላር መሆኑንን የተናገሩት አቶ መስፍን ጣሰው ገቢውም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲተያይ የ8 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል፡፡ በጊዜ ማዕቀፍ 10 አዳዲስ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድን መቀላቀላቸው የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሶስቱ ኤርባስ A350-1000 መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ በዘጠኝ ወሩ ውስጥ አራት አዳዲስ የበረራ መዳረሻዎችንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መክፈቱን ጠቅሷል፡፡ አየር መንገዱ የፊታችን እሁድ ጁን 1, 2025 ከአዲስ አበባ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬት ሻርጃህ ከተማ…
Read More
የአፍሪካ ኢንሹራንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

የአፍሪካ ኢንሹራንስ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

57 በመቶ የሚሆኑት የአፍሪካ ሀገራት ለከፍተኛ የእዳ ችግር መጋለጣቸው ተገልጿል። እነዚሁ ታዳጊ ሀገራት በተያዘው ዓመት ብቻ ከ 80 ቢሊዮን ዶላር በላይ የዉጪ እዳ እንዲከፍሉ ይጠበቃል በአፍሪካ የሕዝብ ዕዳ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት አስታውቋል ። እንደ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ በአህጉሪቱ ከሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት መካከል 57% የሚሆኑት በዕዳ ችግር ውስጥ ገብተዋል ወይም ከፍተኛ የዕዳ ስጋት ላይ ይገኛሉ። ይህንን አኃዝ የገለጹት የድርጅቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ፓቲ ማርቲን በአዳስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘዉ 51ኛዉ የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት ዓመታዊ ኮንፍረንስ እና ጠቅላላ ጉባኤ መድረክ ላይ ሲሆን :- በዚህ ንግግራቸው የዕዳው ጫና መጨመር ዋና ዋና መንስኤዎች የዓለም አቀፍ የገበያ መዋዠቅ እና…
Read More
አሜሪካ ፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም እቅዳቸውን እንዲያሳውቁ ጠየቀች

አሜሪካ ፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም እቅዳቸውን እንዲያሳውቁ ጠየቀች

አሜሪካ ዛሬ አዲስ አበባ ባለው ኤምባሲዋ በኩል ለፌዴራል መንግሥት እና ለታጣቂዎች መልዕክት አስተላልፋለች። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት በመላው ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለጉዳት የዳረጉ ግጭቶች ሰላማዊና ትክክለኛ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። አምባሳደሩ፥ ለታጣቂ ኃይሎች እና ለፌደራል መንግስት ባስተላለፉት መልዕክት ህዝብን እንዲያስቀድሙ ጥሪ አቅርበዋል። " ጦርነቱን ማቆም፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መርዳት እና ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ እና የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል። " በትጥቅ ትግል ስም የሚፈጸሙ ህገወጥ እና የኃይል እርምጃዎች ሊቆሙ ይገባል " ብለዋል። አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በመልዕክታቸው ለፋኖ ፣ ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) እና ለፌደራል መንግስት የተናጠል መልዕክት…
Read More
መንግሥት ሐኪሞች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ኢሰመኮ አሳሰበ

መንግሥት ሐኪሞች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ኢሰመኮ አሳሰበ

በሕክምና ተቋማት በመካሄድ ላይ ያሉ የሥራ ማቆም አድማዎች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በር እንዳይከፍቱ ትኩረት እንዲሰጣቸውም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሕክምና ባለሙያዎች በሕክምና ተቋማት ውስጥ በማድረግ ላይ የሚገኙት የሥራ ማቆም አድማ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳያስከትሉ ትኩረት ሊሰጣቸው እና አፋጣኝ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ ያሳስባል። ኢሰመኮ አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች የደመወዝ እና ከሥራ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን መንግሥት እንዲመልስ ሰጥተናል ያሉት የ30 ቀናት የጊዜ ገደብ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁን ተከትሎ በመንግሥት እና በሕክምና ባለሙያዎች በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃዎች በመከታተል ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሠረት ኢሰመኮ…
Read More