23
Sep
ሀገር በቀሉ ጊቭ ዋተር የተሰኘው ድርጅት ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብት በማሰባሰብ ከ200 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያንን ንጹህ የመጠጥ ውሀ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል። የድርጅቱ ሀብት ማሰባሰብ ኃላፊ አቶ ከማል አህመድ እንዳሉት ድርጅቱ ከተመሰረተበት 2010 ጀምሮ ላለፉት 15 ዓመታት በንፁህ የመጠጥ ውሃ እጦት ክፉኛ እየተፈተኑ ላሉ የገጠር ማህበረሰብ አካባቢዎች የተለያዩ እና በርካታ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ህበረተሰቡን ተጠቃሚ መደረጉን ገልፀዋል። ጊቭ ዎተር በ15 ዓመታት የልማት ጉዞው የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶች መካከል አንዱ በሆነው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ዘርፍ የገጠሩን ማህበረሰብ የትኩረት ማዕከሉ በማድረግ ሲንቀሳቀስ ቆይቷልም ብለዋል። ድርጅቱ በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ሃብት በማሰባሰብ በ 7 ክልሎች በተለይም በአፋር፣ ሶማሌ፣…