Bishoftuairport

የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን ለመገንባት ከስምንት በላይ ሀገራት እየተፎካከሩ ነው ተባለ

የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን ለመገንባት ከስምንት በላይ ሀገራት እየተፎካከሩ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ የቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መንገደኞችን ከማስተናገድ አንጻር እቅሙ ተዳክሟል በሚል ምክንያት በ12 ቢሊዮን ዶላር አዲስ ኤርፖርት ለመገንባት ማቀዷ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በ12 ቢሊዮን ዶላር ለመገንባት የዲዛይን ስራው ተጠናቆ የተቋራጭ ድርጅቶች መረጣ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚህ ኤርፖርት ግንባታ የመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ዓለም አቀፍ ተቋራጮች እንዲወዳደሩ ዓለም አቀፍ የመጀመሪያ ዙሪ ማስታወቂያ መውጣቱን ተከትሎ የአሜሪካ ፣ አውሮፓ ፣ እስያ እና ሌሎችም ሀገራት ፍላጎታቸውን አሳውቀዋል። በዚህም መሰረት የቻይና የግንባታ ተቋማት በብዛት ፍላጎታቸውን እንዳሳዩ ተገልጿል። በቀረበው የእጩዎች ዝርዝር መሰረት ከወጡት አራት ዋና ዋና የሥራ ክፍሎች  ውስጥ የቻይና ተቋማት በተናጠልና በቅይጥ በብዛት ተካተዋል። የቻይና ኮሙኒኬሽንስ ኮንስትራክሽን ኩባንያ (CCCC)፣​ቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያሳድግ ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓመታዊ ገቢውን ወደ 25 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያሳድግ ገለጸ

አየር መንገዱ ከ10 ዓመት በኋላ ዓመታዊ ገቢውን 25 ቢሊዮን ዶላር የማድረስ እቅድ እንዳለው አስታውቋል። ከ10 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ 25 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ፡፡ አቶ መስፍን እንደገለጹት አየር መንገዱ እ.ኤ.አ በ2035 ላይ 209 ዓለም አቀፍ እና 31 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች፣ 271 አውሮፕላኖች እንደሚኖሩትም ጠቅሰዋል፡፡ አየር መንገዱ 67 ነጥበ 2 ሚሊዮን መንገደኞችንም በማጓጓዝ ከ10 ዓመት በኋላ ገቢውንም 25 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም አዳዲስ መዳረሻዎችን በማስፋት ትስስሩን ይበልጥ ማጠናከር እና አዳዲስ መዳረሻዎችን መክፈት የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህም አሁን በረራ ከሚደረግባቸው አምስቱ ክፍለ አኅጉሮች ተጨማሪ አውስትራሊያንም የሚጨመር መሆኑን…
Read More