05
Feb
በ2016 በጀት ዓመት ሥድስት ወራት 100 ሚሊየን ዶላር ማጣቱን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር አስታውቋል። የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ፀሐፊ እንዳለ ሰይፉ፥ ባለፉት ሥድስት ወራት 124 ሚሊየን ዶላር ከቆዳ ምርቶች ሽያጭ ለማግኘት ታቅዶ መሰራቱን ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ማሳካት የተቻለው 14 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ብቻ መሆኑን ተናግረው በግማሽ ዓመቱ የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል። የቆዳ ዘርፉ ከ2010 ዓ.ም በኋላ ባሉት ተከታታይ ዓመታት ከፍተኛ የገቢ ማሽቆልቆል እንዳጋጠመውም አስረድተዋል። የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የሥራ ማስኬጃ በጀት እጦትና ለዘርፉ የተሰጠው የትኩረት ማነስ ለገቢው መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል። በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያትም የቆዳ ፋብሪካዎች ከሥራ…