Business

ሶማሊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በግዛቷ እንዳያርፍ ከለከለች፡፡

ሶማሊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በግዛቷ እንዳያርፍ ከለከለች፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና በራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከሶስት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። ስምምነቱ ኢትዮጵያ በኤደን ባህረ ሰላጤ 20 ኪሎሜትሮች የሚረዝም የባህር ጠረፍ እንድትከራይ እና በምትኩ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንድትሰጥ የሚያስችል ነው። ይህ ስምምነት ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የበረራ ቁጥሩ ET8372 የተሰኘ አውሮፕላን ወደ ራስ ገዟ ሶማሊላንድ በዛሬው ዕለት በረራ በማድረግ ላይ እያለ እንዲመለስ መደረጉ ተገልጿል፡፡ የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በቀድሞ ስሙ ትዊተር አሁን ኤክስ አካውንቱ ይፋ እንዳደረገው የግዛቴ አካል ናት ወደ ሚላት ሶማሊላንድ ሀርጌሳ እየበረረ የነበረ አውሮፕላን እንዳያርፍ…
Read More
የኢትዮጵ አየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ ጀመረ

የኢትዮጵ አየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ ጀመረ

አየር መንገዱ በአፍሪካ ያሉትን የጭነት መዳረሻዎች ብዛት ወደ 35 አሳድጓል። ወደ ካዛብላንካ የሚደረገው የጭነት በረራ ከ100 ቶን በላይ የመሸከም አቅም ባለው ቦይንግ 777-200F የእቃ ጭነት አውሮፕላን ነው ተብሏል። የኢትዮጵ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው “ወደ ካዛብላንካ ሞሮኮ አዲስ የጭነት በረራ አገልግሎት መስጠት በመጀመራችን ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል በመልዕክታቸው። ይህ በረራ መጀመሩ በአፍሪካ ያለንን የዕቃ ጭነት መዳረሻ ቁጥር 35 ሲያደርስ፤ በተመሳሳይ ብሔራዊ አየር መንገዱ በእቃ ጭነት አገልግሎት ዘርፍ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ እንደሆነ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭነት በረራ መዳረሻዎች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ እና በዓለም የአየር የዕቃ ጭነት አገልግሎት መስክ ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኝ…
Read More
ኢትዮጵያ በቮልስዋገን ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

ኢትዮጵያ በቮልስዋገን ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

በቮልስ ዋገን አይዲ ሲሪየስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱ ተገልጿል፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ቮልስ ዋገን አይዲ ሲሪየስ (ID Series) የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ እገዳ ጥላ ነበር፡፡ ከቻይና ተገጣጥሞ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የነበረው የጀርመን ምርት የሆነው ቮልስ ዋገን ተሽከርካሪ ባትሪው ከኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጋር የሚጣጣም አይደለም በሚል በቀረበው ቅሬታ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ታግዶ ቆይቷል፡፡ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሕዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪና ተሽከርካሪ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አበራ ሞሲሳ እንዳሉት፤ የጀርመን መንግሥት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ መሠረት ቮልስ ዋገን ተሽከርካሪ እንዳይገባ ተደርጎ ቆይቷል፡፡ ደብዳቤው የተሽከርካሪዎች ባትሪ ከኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጋር የማይጣጣም…
Read More
በኢትዮጵያ ከ20 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በሐሰተኛ ሰነዶች እንደሚኖሩ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከ20 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በሐሰተኛ ሰነዶች እንደሚኖሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት እንዳስታወቀው የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ሰነዶችን ተጠቅመው ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ፓስፖርት፣ ሀሰተኛ ቪዛ እና ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየኖሩ ይገኛል ብለዋል። በተደረገው የማጣራት ስራ ከ18 ሺህ በላይ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ከ1 ሺህ 500 በላይ ሀሰተኛ ቪዛ እና ከአንድ ሺህ 800 በላይ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያን ያሰሩ ዜጎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መገኘታቸውንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። በመሆኑም ህገወጥ ሰነድ ያለቸው ዜጎች ከጥር አንድ ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም…
Read More
ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን ገለጸች

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን ገለጸች

በቀይ ባህር ላይ ወደብ እንደሚያስፈልጋት ስትገልጽ የቆየችው ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ እንደ ጽህፈት ቤቱ መግለጫ ከሆነ የባህር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌ ላንድ ጋር ተፈራርማለች፡፡ የባህር በር ሊዝ ስምምነቱን ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሌ ላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እንደተፈራረሙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ስምምነት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር በር እንዲኖራት ለያዘችው ጥረት ጥሩ መደላደል ሊፈጥር ይችላልም ተብሏል፡፡ ይሁንና የባህር በር ሊዝ ስምምነቱ ለምን ያህል ጊዜ፣ በምን ያህል ገንዘብ እና የስምምነቱ ዝርዝር መረጃ እስካሁን በማንኛውም ወገን ይፋ አልተደረገም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከወራት በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት…
Read More
ኢትዮጵያ በሕገ- ወጥ እንስሳት ንግድ ምክንት በየወሩ 17 ሚሊዮን ዶላር እያጣች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በሕገ- ወጥ እንስሳት ንግድ ምክንት በየወሩ 17 ሚሊዮን ዶላር እያጣች ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በቀን ከ1 ሺህ 200 በላይ የቁም እንስሳት በሕገ-ወጥ መንገድ ከአገር በመውጣታቸው በየቀኑ ከ630 ሺህ ዶላር በላይ እንደምታጣ ተገልጿል። በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለአገልግሎት የሚወሉ መድኃኒቶችም የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው በጤና ሥርዓቱ ላይ ጫና እያሳደሩ መሆኑም ተገልጿል። በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ሕገ-ወጥ ንግድን መከላከል ላይ ያተኮረ አገር አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ ዛሬ ተካሂዷል። ምክር ቤቱ ሕገ-ወጥ ንግድ በስፋት በሚታይባቸው ዘርፎች ላይ ያካሄዳቸውን ጥናቶች ይፋ አድርጓል። ጥናቶቹ በቁም እንስሳት፣ በመድኃኒት፣ በጨርቃጨርቅ፣ በሎጂስቲክስ ሥርዓት ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችና ንግድን በተመለከቱ የሕግ ማዕቀፎች ላይ የተካሄዱ ናቸው። አሁን ላይ የቁም እንስሳትና የመድኃኒት ሕገ-ወጥ ንግድ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ በጥናቱ ተመላክቷል። በኢንዱስትሪ…
Read More
ዳሸን ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ ቲኬት በብድር መሸጥ ጀመሩ

ዳሸን ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጉዞ ቲኬት በብድር መሸጥ ጀመሩ

ዳሸን ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቅመው ክፍያውን ቆይተው የሚከፍሉበትን አዲስ የክፍያ አማራጭ በጋራ አስተዋውቀዋል። አቶ ዮሃንስ ሚሊዮን የዳሽን ባንክ ዲጂታል ባንኪንግ ዋና መኮንን “ጉዞዎ ይቀድማል ክፍያው ይደርሳል” በሚል የተሰየመው ይህ አገልግሎት በደንበኞች ምርጫ መሰረት በ6 ወር ወይም በ12 ወር የብድር ክፍያ የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል። ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን በዳሸን ባንክ የሂሳብ ቁጥር መክፈት እንደሚገባቸው እና በተጨማሪም በባንኩ ቢያንስ ለሶስት ወራት አገልግሎት ያገኙ መሆን እንደሚኖርባቸውም ጠቁመዋል።  አቶ ዮሃንስ አክለውም አገልግሎቱን ለማግኘት ደንበኞች አቅራቢያቸው ወደሚገኝ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ በሚያመሩበት ወቅት አስፈላጊ ሰነዶችን ማሟላት የሚገባቸው ሲሆን ማስያዣም ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸውም ገልፀዋል። ስምምነቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና…
Read More
አሜሪካ፣ ካናዳ እና ብሪታንያ ኢትዮጵያ የቬና ዲፕሎማቲክ ስምምነት መጣሷ እንዳሳሰባቸው ገለጹ

አሜሪካ፣ ካናዳ እና ብሪታንያ ኢትዮጵያ የቬና ዲፕሎማቲክ ስምምነት መጣሷ እንዳሳሰባቸው ገለጹ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ ያሉ ሁለት የባንኩ ሰራተኞች በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ድብደባ፣ እስር እና እንግልት እንደደረሰባቸው አስታውቆ ነበር። ባንኩ እንዳለው ሁለት ሰራተኞቹ የቬና የዲልሎማሲ ጥበቃ ስምምነትን እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ቢሮ አስተናጋጅ ሀገራት ስምምነትን የጣሰ ክስተት በኢትዮጵያ መፈጸሙንም ገልጿል። የተፈጠረውን ክስተት ለኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ ማመልከቱን የሚገልጸው የአፍሪካ ልማት ባንክ ጉዳዩ መፈጸም እንደሌለበት፣ ህግ መጣሱን እና ጉዳዩ ተመርምሮ እርምጃ እንደሚወሰድ በኢትዮጵያ በኩል ቃል ተገብቶልኛል ሲልም በወቅቱ አስታውቆ ነበር፡፡ ባንኩ አሁን ላይ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል በገባው መሰረት በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዳልወሰደ እና ጉዳዩን ስለመመርመሩ መረጃ እንዳልሰጠው ገልጿል፡፡ የአሜሪካ፣ ካናዳ እና ብሪታኒያ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጡት…
Read More
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል አዲስ ተደራዳሪ ቡድን አዋቀረች

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል አዲስ ተደራዳሪ ቡድን አዋቀረች

የዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ድርድርን እና ቀጣናዊ የንግድ ትስስሮችን የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ በአዲስ መልክ መቋቋሙን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ኮሚቴው ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችን እንዲሁም ባለሙያዎችን ያካተተ ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በተለያዩ ጊዜያት ፍላጎቷን ብታሳይም ከአባል አገራት ለሚነሱ አንዳንድ የንግድ ዘርፍ አካታችነት አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ባለመቻሏ ድርጅቱን መቀላቀል ሳትችል ቆይታለች። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ከአምስት ዓመት በፊት ወደ ስልጣን ሲመጣ የዓለም ንግድን በአባልነት መቀላቀል እንደሚፈልግ በይፋ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ መንግስት ከወሰዳቸው ስር ነቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና አዳዲስ ለውጦች መካከል አገሪቱን በ2021 የአለም ንግድ ድርጅት አባል ማድረግ ይገኝበታል። በዚህም ከ2020 አንስቶ ድርድር እንደ አዲስ…
Read More
ኢትዮጵያ 6 ሚሊዮን ዶላር በስህተት ለሌላ ወገን መክፈሏ ተገለጸ

ኢትዮጵያ 6 ሚሊዮን ዶላር በስህተት ለሌላ ወገን መክፈሏ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ መዋጮ መከፈል የነበረበትን ስድስት ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ በስህተት ወደ ሌላ አካውንት መላኳ ተገልጿል፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ ያሉ ሁለት የባንኩ ሰራተኞች በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ድብደባ፣ እስር እና እንግልት እንደደረሰባቸው አስታውቆ ነበር። ባንኩ እንዳለው ሁለት ሰራተኞቹ የቬና የዲልሎማሲ ጥበቃ ስምምነትን እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ቢሮ አስተናጋጅ ሀገራት ስምምነትን የጣሰ ክስተት በኢትዮጵያ መፈጸሙንም ገልጿል። የተፈጠረውን ክስተት ለኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ ማመልከቱን የሚገልጸው የአፍሪካ ልማት ባንክ ጉዳዩ መፈጸም እንደሌለበት፣ ህግ መጣሱን እና ጉዳዩ ተመርምሮ እርምጃ እንደሚወሰድ በኢትዮጵያ በኩል ቃል ተገብቶልኛል ሲልም በወቅቱ አስታውቆ ነበር፡፡ ባንኩ አሁን ላይ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል በገባው…
Read More