04
Sep
በሁለት አመቱ የትግራይ ጦርነት የተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ጥሪ አቀረበ። የያለፈው ጦርነት እና ጥፋት ተጠያቂነት ባለመረጋገጡ በጦርነቱ ተሳታፊ የነበሩ ሐይሎች ለሌላ ጥፋት እየተዘጋጁ ነው በማለት አረና ከሷል። በወቅታዊ የትግራይ ፖለቲካዊ ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙርያ መግለጫ የሰጠው በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ህወሓት ውስጥ የተፈጠረው መከፋፈል ለትግራይ አደጋ ይዞ የሚመጣ እና ሐላፊነት የጎደለው አካሄድ እየተከተለ ያለ ሲል ገልፆታል። የዓረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ "አሁንም ወደ ጦርነት የሚወስዱ መንገዶች እየታዩ ያሉት እና የጦርነት ነጋሪት የሚጎሰመው ባለፈው 2 ዓመት ለነበረው ጦርነት ከሁሉም ወገን ተጠያቂነት ባለመረጋገጡ ነው፤ ከህወሓት ይሁን ከሻዕብያ እንዲሁም ብልፅግና ወገን የጦርነቱ…