11
Apr
የብሪታንያ ንግድ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ብሪታንያ የአበባ ምርቶችን ወደ ሀገራቸው በሚያስገቡ ነጋዴዎች ላይ ጥላው የነበረውን ግብር አንስታለች፡፡ ሀገሪቱ ከዚህ በፊት የአበባ ምርቶች ወደ ብሪታንያ ሲገቡ 8 በመቶ ግብር መክፈል የነበረባቸው ሲሆን ከዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ማንሰቷን አስታውቃለች፡፡ የብሪታንያ ንግድ ኮሚሽነር ጆን ሀምፍሬይ እንዳሉት ወደ ብሪታንያ የሚገቡ የአበባ ምርቶች ከግብር ነጻ መሆናቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አበባ አምራች እና ነጋዴዎችን ተጠቃሚ ከማድረጉ ባለፈ በብሪታንያ የአበባ ምርት በቅ አቅርቦት እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ፣ኬንያ፣ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል አበባ ላኪ ሀገራት ናቸው፡፡ እነዚህ አምስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በቀጥታም ይሁን በሶተኛ ሀገር አድርገው ወደ ብሪታንያ ለሚያስገቡት የአበባ ምርት የገቢ…