Mekicity

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ

የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንትና ለሊት በመቂ ከተማ መገደላቸው ተገልጿል። "ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው ተገድለው ነው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል" ሲል ፓርቲያቸው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኢነግ በመግለጫው አክሎም አቶ በቴ ኡርጌሳ ከህግ ውጪ በተፈጸመባቸው ግድያ ህይወታቸው ማለፉን ገልጾ ግድያው የኦሮሞን ጥያቄ ለማፈን እና አመራር አልባ ለማድረግ ነው ሲልም ገልጿል፡፡ በኦሮሞ ህዝብ የሚወደዱ ሰዎችን እያሳደዱ መግደል ቀጥሏል ያለው ኦነግ ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ተገድሎ እስካሁን ፍትህ አልተጠም ሲልም ፓርቲው አክሏል፡፡ አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት " ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል…
Read More